አማራ ክልልአዊ ዞንዚገም ወረዳ የምትገኘዋን የቅላጅ ከተማ ታሪካዊ አመሠራረትና አጠቃላይ ገፅታ በከፊል

የከተማ ታሪካዊ አመሰራረት

ለማስተካከል

ኢትዮጵያ ሀገራችን ቀደምነት ታሪክ ካለቸው ከተሞች አመሰራረት ከታየባቸው ሀገሮች አንዷ ነች። ነገር ግን ኢትዮጵያ ቀደምነት ያላቸው ከተሞች የታዩበት ሀገር ትሁን እንጂ ከራሷ የእድገት ሁኔታ ጋር በተያየዘ የከተሞች እድገት እስከ 20ኛው ክፍለ ዘመን የመጀመሪያ ድረስ ከዚህ ግባ በሚባል አልነበረም። ነገር ግን ስልጣኔ ወደ ሀገራችን መግባት ከጀመረበት ከ19ኛው ክፍለ ዘመን ማብቄያ አካባቢ ጣሊያን ሀገራችን ከወራራበት ጊዜ ጀምሮ በርካታ ከተሞች መቆራቆር እንደ ጀመሩና እድገታቸውም በዚያው ልክ እያደገ እንደሄደ የተለያዩ ጥንታዊ ፅሑፎች ያስረዳሉ። ታሪክን ማወቅ ያለፈው ትውልድ የሰራቸውን መልካም ነገሮችን ቀምሮና የአሁኑና ሞች ትውልድ በአግባብ እንዲጠቅምባቸው ለማድረግ መጥፎዎች ደግሞ ታሪክ ሁነው እንዲቀሩ ለማድረግ ይረዳል። ከዚህ አንፃር የቅላጅ ከተማን ቀደምት ታሪክ በመደሰስ ከተማዋ የት ተነስተ የት እንዳደረሰች በታሪኩ መዘክርነትነት የመቀመጥ ቅርስ ማስቀመጥ ታሪክን ለማወቅና ወደ ፊት በከተማዋ ላይ ሰፋ ያለ ጥናት ለሚዘጋጅ መነሻ እንዲሆን ለማሳወቅ የፅሑፍ ማስረጃ ከሀገር ሽማግሌዎች በመጠየቅና ውይይት ማድረግ የከተማዋን ታሪክ ለመደሰስ ሞክረናል። ከተማዋ እንቅስቃሴ የጀመረችው በንግስት ዘውዲቱ ዘመነ መንግስት ቢሆንም በይፋ የተመሰረተችው ግን በአፄ ኃይለ ስላሴ ዘመነ መንግስት የዚገም ምክትል ወረዳ ገዢ በነበሩበት በፊታውራሪ ደረሶ ተሰማ በ1925 ዓ/ም እንዳሆነ አረጋዊያን ያስረዳሉ። በዝርዝር ታሪኳም እንዲህ ነው። የዚገም ግዛት በምስራቅ በኩል ከዳሞት ግዛት ጋር ይወስን ነበር። በሁለቱም ግዛቶች ድንበር ጫፍ ላይ ደግሞ አካኮ የምትበል ገበያ ነበረች። ይህች ገበያ በርካታ ገቢ የተገኘው ከዚገም እና ከዳሞት ግዛት እየመጡ ይገበያዩበት የነበረች ሲሆን በሁለቱም ድንበርተኞች አጎራባች ግዛቶች ማዕከል በሚነሳ ግጭት/አለማግባባት/ ዳሞቶች ገበያ መጠው የዚገም ሰው ገድሎ ድንበራቸው ቅርብ ስለነበረ ወደ ዳሞት ግዛት ይገባሉ። ዚገሞች ከሠው ግዛት ቢገቡ የሰው ግዛት ጥሶ ለገቡ ዋስትና የለም። የዚገሞች እንዲህ ከዳሞት የመጣን ገበያተኞች ገድሎ ወደ ራሳቸው ግዛት ይመጣሉ። ዳሞቶች የሰው ግዛት ጥሶ ቢገቡ ከላይ የተጠቀሰው ዕጣ ይገቡና ሟቹ ካልሆነም የአካኮ ገበያ በድንበር ላይ መሆን ከገበያ ማዕከልነት ባለፈ የግጭት ማዕከል የሆነችው ከመምጣቷ ፊታውራሪ ደረሶ ተሰማ ገበያውን ከነበረችበት በመነሳት እና ማክሰኞ ትውል የነበረችውን የማቻ ገበያ በአንድ ላይ በማድረግ አሁን ዋና ገበያው ከሚገኝበት የከተማዋ ደቡብ ጫፍ ላይ ቅዳሜ ቅዳሜ ቀን እንዲውል አድርጓል። በ1925 ዓ/ም ገበያውን እንደመሰረቱትና ከተማዋ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ በይፋ እንደተመሰረተችው የከተማዋ ዕድ ጠቢብ አዛውንቶች በሰፊው ያስረዳሉ። ከተማዋም ከተመሰረተች ጊዜ ጀምሮ ምክትል ግዢ ደረጃነትን ይዛ እንደነበረች የፓርላማ ተወካይ እንደነበሩት ያስረዳሉ። የዚገም ምክትል ግዢ የነበሩት ፊታውራሪ ደረሶ ተሰማ ልጅ ልጅ ተሰማ ደረሶ ቅላጅ ከተማ የመጀመሪያ የፓርላማ ተወካይ ሁነው እንደተመረጡም አዛውንቶች በትዝታ ያስታውሳሉ።