ቃልም እግዚአብሔር ነበረ ------> ቃልም ሥጋ ሆነ ስለዚህ እየሱስ እግዚአብሄር ነው ብለህ ካመንክ ኢሄን አንብበው እስቲ ፦

‘በፊትህ መንገድህን ያዘጋጅልህ ዘንድ፣ ከአንተ አስቀድሜ መልእክተኛዬን እልካለሁ።’

ማቴዎስ 11 : 7 የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት ከሄዱ በኋላ፣ ኢየሱስ ለሕዝቡ ስለ ዮሐንስ እንዲህ ሲል ተናገረ፤ “ወደ ምድረ በዳ ምን ልታዩ ወጣችሁ? ሸምበቆ በነፋስ ሲወዛወዝ? 8 ወይስ ምን ልታዩ ወጣችሁ? ባማረ ልብስ ያጌጠ ሰው? ባማረ ልብስ ያጌጡ በነገሥታት ቤት አሉላችሁ። 9 ታዲያ ምን ልታዩ ወጣችሁ? ነቢይ ልታዩ? አዎን፤ ከነቢይም የሚበልጥ ነው። 10 እንዲህ ተብሎ የተጻፈለት እርሱ ነው፤ “ ‘በፊትህ መንገድህን ያዘጋጅልህ ዘንድ፣ ከአንተ አስቀድሜ መልእክተኛዬን እልካለሁ።’


‘በፊትህ መንገድህን ያዘጋጅልህ ዘንድ፣ ከአንተ(ከእየሱስ) አስቀድሜ መልእክተኛዬን(ዮሀንስን) እልካለሁ።’(ላኪው ማነው ፈጣሪ ወይም እግዚአብሄር ነው)

(“ ‘በፊቴ መንገዴን ያዘጋጅልኝ ዘንድ፣ ከእኔ አስቀድሜ መልእክተኛዬን እልካለሁ።’ ብሎ ቢሆን ኖሮ እየሱስ እራሱ እግዚአብሄር ነው የሚለው ሀሳብ ትክክል ይሆን ነበር፡፡ ነገር ግን ፦ “ ‘በፊትህ መንገድህን ያዘጋጅልህ ዘንድ፣ ከአንተ አስቀድሜ መልእክተኛዬን እልካለሁ።’ ነው ያለው)

ዮሀንስ 1 :6 ከእግዚአብሔር የተላከ ዮሐንስ የተባለ አንድ ሰው ነበረ። 7 ሰዎች ሁሉ በእርሱ በኩል እንዲያምኑ፣ ስለ ብርሃን ምስክር ሆኖ ለመቆም መጣ፤ 8 ስለ ብርሃን ሊመሰክር መጣ እንጂ እርሱ ራሱ ብርሃን አልነበረም።

ዮሀንስ 1 :32 ከዚያም ዮሐንስ እንዲህ ሲል ምስክርነቱን ሰጠ፤ “መንፈስ እንደ ርግብ ከሰማይ ወርዶ በእርሱ ላይ ሲያርፍ አየሁ፤ 33 በውሃ እንዳጠምቅ የላከኝም፣ ‘በመንፈስ ቅዱስ የሚያጠምቀው፣ መንፈስ ሲወርድና በርሱ ላይ ሲያርፍ የምታየው እርሱ ነው’ ብሎ እስከ ነገረኝ ድረስ እኔም አላወቅሁትም ነበር፤

በውሃ እንዳጠምቅ የላከኝም (እግዚአብሄር)፣ ‘በመንፈስ ቅዱስ የሚያጠምቀው(እየሱስ)፣ መንፈስ ሲወርድና በርሱ ላይ ሲያርፍ የምታየው(እየሱስን ማለቱ ነው) እርሱ ነው’ ብሎ እስከ ነገረኝ ድረስ(የነገረኝ እግዚአብሄር) እኔም(ዮሀንስ ነኝ) አላወቅሁትም ነበር፤

እንደዚህ ከሆነ እየሱስ እግዚአብሄርን ሊሆን የሚችለው እንዴት ሆኖ ነው?????? እየሱስ እራሱ እግዚአብሄርን ሊሆን የሚችለው እንዴት ነው?????????