ቃላት (Qalat) በካናዳ ሀገር በደራሲና ዳይሬክተር ዮናስ ኃይለመስቀል ኪዳኔ የተሰራ ልብ አንጠልጣይ አማርኛ ፊልም ነው። ፊልሙ በሁለት ጓደኞች ላይ ሲያጠነጥን የተመረቀውም በጳጉሜ 03 ቀን 2016አም. በቶሮንቶ ከተማ በአርሜንያ ወጣቶች ማእከል ላይ ነው።