ቀላዋ (Maesa lanceolata) ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኝ ተክል ነው።

ቀላዋ

የተክሉ ሳይንሳዊ ጸባይEdit

ትልቅ ቊጥቋጦ እስከ 7 ሜትር ይደርሳል። ታላላቅ ቅጠልና ቀይ-ቡናማ ልጥ አለው። ቅጠሉ ቢሰበር ቡናማ ሙጫ ይወጣል።

አስተዳደግEdit

በብዛት የሚገኝበት መልክዓ ምድርEdit

በደጋ ጫካዎች ተራ ነው። በፈሳሽ ዳርና በጫካ ዳር ይገኛል። በአፍሪካ፣ ደቡብ አረቢያና ማዳጋስካር ይገኛል።

የተክሉ ጥቅምEdit

ቢጫ ክብ ፍሬዎች ዘይት ይሰጣል፣ ይህም ዘይት አዲስ ሸክላ ለመደፈን ትልንም ለመግደል ይጠቀማል።

የቅጠሉ ውጥ ለአሣ መርዝ ነው፤ ዛጎል ለበስንም ይገድላል።[1]

የኮሶ ትልን ለማስወጣት፣ የቀላዋ ሥር ተደቅቆ በውሃ ይጠጣል።

እባብ ነከስ፣ የቀለዋ ቅጠል ይኘካል።[2]


  1. ^ አማረ ጌታሁን - SOME COMMON MEDICINAL AND POISONOUS PLANTS USED IN ETHIOPIAN FOLK MEDICINE Archived ጁላይ 31, 2017 at the Wayback Machine March 1976 እ.ኤ.አ.
  2. ^ በደብረ ሊባኖስ ዙሪያ ያለው ሕዝብ መድሃኒታዊ እጾች እውቀናና ጥቅም 1998 ዓም ከጥላሁን ተክለሃይማኖት፣ ሚሩጸ ጊዳይ፣ ግርማይ መድኅን፣ ያለም መኮነን፣ አዲስ አበባ ዩኒቬርሲቴ፣ አክሊሉ ለማ ተቋም