ሺስቶሶሚሲስ
ይህ መጣጥፍ ከተመሳሳዩ መጣጥፍ ከቢልሃርዝያ ጋራ እንዲዋሐድ የሚል ሀሣብ ቀርቧል። (ውይይት) |
ሺስሰቶሶሚያሲስ (ቢልሃርዚያ እና ካታያማ ትኩሳት በመባል ይታወቃል፡፡)[1][2] በሽታው የሚተላለፈው ጥገኛ ትላትሎች በሆነው የ ሺስቶሶማ የህዋስ አይነት ነው፡፡ የ ሽንት መተላለፊያ ወይም አንጀት ሊያጠቃ ይችላል። የህመሙ ምልክት የሆድ ህመም፣ ተቅማጥ፣ ደም የተቀላቀለበት ሰገራ ወይም በሽንት ላይ ደም መታየትን ያጠቃልላል። ለረጅም ጊዜ ህመሙ የቆየበት ሰው የጉበት ህመም፣ የኩላሊት ስራ ማቆም፣ መሃንነት ፣ ወይም የፊኛ ካንሰር ሊያስከትብ ይችላል፡፡ በልጆች ላይ ዝቅተኛ እድገትና የመማር ችግር ሊያስከትል ይችላል። [3]
ቢልሃርዝያ
ድራኩንሱሊአሲስ | |
---|---|
Classification and external resources | |
ICD-10 | B65 |
ICD-9 | 120 |
MedlinePlus | 001321 |
MeSH | D012552 |
በሽታው የሚሰራጨው ትላትሎቹ ያሉበት ውሀ ላይ በሚፈጠር የቆዳ ንክኪ ነው። እነዚህ ትላትሎች የሚመነጩት ከተበከሉ ቀንድ አውጣዎች ነው፡፡ ይህ በሽታ በታዳጊ ሀገራት በሚነኙ ታዳጊዎች ላይ የተለመደ ሲሆን ምክንያቱም ልጆቹ በተበከለ ውሃ የመጫወታቸው አጋጣሚ ሰፊ በመሆኑ ነው፡፡ ሌላው ደግሞ በእለት ከእለት ስራ አማካኝነት ማለትም ገበሬዎች፣ አሳ አጥማጆችና ሌሎች የተበከለውን ውሀ የሚጠቀሙ ሰዎች የበሽታው ስጋት የሚያጠቃልላቸው ቡድኖች ናቸው። [3] ሄልመንት በሽታዎች በሚባለው ቡድን ውስጥ ይጠቃለላሉ። [4] ምርመመራው የሚደረገው የትሉን እንቁላሎች በሽንት ወይም ሰገራ ላይ በመመርመር ነው፡፡ በደም ላይ ፀረ እንግዳ አካል በመፈለግ ማረጋገጥም ይቻላል። [3]
በሽታውን የመከላከያ መንገድ ንፁህ ውህ አቅርቦትን ማሻሻልና የቀንድኣውጣ ቊጥርን መቀነስ ነው፡፡ [3] --> በሽታው በተስፋፋበት ቦታ በአንድ ጊዜ ሁሉምን ሰዎች ፕራዚኩዋንትል በተባለ መድኃኒት በአየዓመቱ ማከም ያስፈልጋል። ይህ በበሽታው የሚያዙትን ቊጥር ለመቀነስና የበሽታውን ስርጭት እንዲቀንስ ያደርጋል። ፕራዚኩዋንትል በበሽታው የተጠቁትን ለማከም በ World Health Organization የሚመከር የህክምና ዘዴ ነው፡፡ [3] በሽታውን ለመከላከል ሕዝቡ ሽንቱንና ሰገራውን የሚጠጣው ውሃ፣ ኩሬ ወይም ወንዝ ውስጥ እንዳያደርግ ማስተማረ ነው። የትሉ እንቁላቆች በሽንትና ሰገራ ከስው ውስጥ ወጥተው ቀንድ ኣውጣ ውስጥ ገብተው እንደሚባዙ መግለጽ ነው። ዶክተር ኣክሊሉ ለማ እንዶድ ቀንድኣውጣን እንደሚገድል ስለደረሱበት በሽታውን ለመከላከል ትልቅ ኣስተዋጽዖ ኣድርገዋል።
ሲስቶሶሚያሲስ በዓለም ላይ ወደ 210 ሚሊየን የሚጠጋ ሕዝብ ያጠቃል፣ [5] እንዲሁም የሚገመተው ከ 12 000 [6] እስከ 200,000 የሚሆነው ሕዝብ በአመት ውስጥ ይሞታል ተብሎ ይገመታል፡፡ [7] በሽታው በስፋት የሚታየው በ አፍሪካ ፣ እንዲሁም በ እስያ ና ደቡም አሜሪካ ነው። [3] ወደ 700 ሚሊዮን የሚሆን ሕዝብ፣ ከ70 በላይ ሃገራት፣ በሽታው በስፋት በተሰራጨበት አካባቢ ይኖራል፡፡ [7][8] ሲስቶሶሚሲሰ ከወባ ወይም ማላሪያ ቀፅሎ በሁለተኛነት ያለ፣ እንደ ትላትል ትልቅ የኢኮኖሚ ተፅእኖ ያለው በሽታ ነው። [9] ከጥንት ጀምሮ እስከ 20ኛው ክፍለ ዘመን ድረስ፣ ሲስቶሶሚሲሰ የ በሽንት ውስጥ ያለ ደም ምልክት የሚታየው በስሕተት እንደ የወንድ አይነት ወር አበባ እየተባለ በ ግብፅ እናም ለወንዶች ልጆች እንደ rite of የአምልኮ መተላለፊያ ተደርጎ ይታይ ነበር፡፡ [10][11] የሚመደበው ችላ ከተባሉት የትሮፒካል በሽታ ስር ነው። ref>"Neglected Tropical Diseases" (June 6, 2011). በ28 November 2014 የተወሰደ.</ref>
ቢልሃርዚያ ጣና ሃይቅ ውስጥ ኣለ ይባላል።
References
ለማስተካከል- ^ "Schistosomiasis (bilharzia)". NHS Choices (Dec 17, 2011). Archived from the original on 15 March 2014. በ15 March 2014 የተወሰደ.
- ^ "Schistosomiasis" (12/02/2013). Archived from the original on 23 May 2015. በ11 June 2014 የተወሰደ.
- ^ ሀ ለ ሐ መ ሠ ረ "Schistosomiasis Fact sheet N°115". World Health Organization (February 2014). በ15 March 2014 የተወሰደ.
- ^ "Chapter 3 Infectious Diseases Related To Travel" (August 1, 2013). በ30 November 2014 የተወሰደ.
- ^ Fenwick, A (Mar 2012). "The global burden of neglected tropical diseases.". Public health 126 (3): 233–6. doi:10.1016/j.puhe.2011.11.015. PMID 22325616.
- ^ Lozano, R; Naghavi, M; Foreman, K; Lim, S; Shibuya, K; Aboyans, V; Abraham, J; Adair, T et al. (Dec 15, 2012). "Global and regional mortality from 235 causes of death for 20 age groups in 1990 and 2010: a systematic analysis for the Global Burden of Disease Study 2010". Lancet 380 (9859): 2095–128. doi:10.1016/S0140-6736(12)61728-0. PMID 23245604.
- ^ ሀ ለ Thétiot-Laurent, SA; Boissier, J; Robert, A; Meunier, B (Jun 27, 2013). "Schistosomiasis Chemotherapy". Angewandte Chemie (International ed. in English) 52 (31): 7936–56. doi:10.1002/anie.201208390. PMID 23813602.
- ^ "Schistosomiasis A major public health problem". World Health Organization. በ15 March 2014 የተወሰደ.
- ^ The Carter Center. "Schistosomiasis Control Program". በ2008-07-17 የተወሰደ.
- ^ Kloos, Helmut; Rosalie David (2002). "The Paleoepidemiology of Schistosomiasis in Ancient Egypt" (PDF). Human Ecology Review 9 (1): 14–25. http://www.humanecologyreview.org/pastissues/her91/91kloosdavid.pdf.
- ^ Rutherford, Patricia (2000). "The Diagnosis of Schistosomiasis in Modern and Ancient Tissues by Means of Immunocytochemistry". Chungara, Revista de Antropología Chilena 32 (1). ISSN 0717-7356. http://www.scielo.cl/scielo.php?pid=S0717-73562000000100021&script=sci_arttext.