ሶዶ ዙሪያ ወረዳ ወላይታ ዞን ከሚገኙ ወረዳዎች አንዱ ነው። ወረዳው በስተምዕራብ በኪንዶ ኮይሻ ወረዳ፥ በበስተሰሜን በቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ፥ በስተሰሜን ምሥራቅ በዳሞት ጋሌ ውረዳ፥ እንዲሁም ደግሞ በበስተደቡብ ምዕራብ በኦፋ ወረዳ ይዋሰናል።

የህዝብ ቁጥር ለማስተካከል

በ1999 ዓ.ም በማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ በተደረገው ህዝብ ቆጠራ መሰረት በወረዳው በአጠቃላይ 162,691 ሰው የሚኖር ሲሆን፥ ከነዚህም 80,002 ወንድ ሲሆኑ 82,689 ደግሞ ሴት ናቸው፤ ማናቸውም የከተማዊ አይደሉም። በሶዶ የወረዳዉ ዋና መቀመጫ ነው። የሚበዙት የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ ሲሆኑ፥ 66.67% ያህሉን ይይዛሉ፤ 26.83% የሚሆኑት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያን እና 5.28% የሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታይ ናቸው።[1]

በ1986 ዓ.ም በማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ በተደረገው ህዝብ ቆጠራ መሰረት በወረዳው ከወላይታ (92.81%) በተጨማሪ፣ አማራ ብሔር (2.6%)፥ ጋሞ (0.85%)፥ ዶርዜ (0.77%) እና ስልጤ (0.76%) እንዲሁም ሌሎችም ብሔር ብሔረሰቦች (2.21%) ይገኙበታል።[2]

ዋቢ ለማስተካከል

  1. ^ Census 2007 Tables: Southern Nations, Nationalities, and Peoples' Region Archived ኖቬምበር 13, 2012 at the Wayback Machine, Tables 2.1, and 3.4.
  2. ^ 1994 Population and Housing Census of Ethiopia: Results for Southern Nations, Nationalities, and Peoples' Region, Vol. 1, part 1 Archived ኖቬምበር 19, 2008 at the Wayback Machine, Tables 2.1, 2.12, 2.15, 2.19 (accessed 30 December 2008)