የስፓይሩሊና ምንነትና ጥቅሞች ለማስተካከል

 
የስፓይሩሊና ምስል

ስፓይሩሊና ምንድነው? ለማስተካከል

ስፓይሩሊና የሚለው ስም የተወሰደው ከላቲን ቃል ሲሆን ትርጓሜውም ቀጭን ጥምዝምዝ ማለት ነው፡፡ ስፓይሩሊና በዋነኛነት ከሁለት የሲያኖባክቴሪያ ዓይነቴዎች ማለትም ከአርትሮስፒራ ፕላተንሲስና አርትሮስፒራ ማክሲማ የሚዘጋጁ የሰው ምግብና የእንስሳት ተጨማሪ ምግቦች የሚታወቁበት ስም ነው፡፡

ሌሎች የአርትሮስፒራ ዓይነቴዎች በስፓይሩሊና ዝርያ ስር ተመድበው እንደነበር ይታወቃል፡፡ በአሁኑ ጊዜ በተደረገ ስምምነት ሁለቱም (ስፓይሩሊናና አርትሮስፒራ) ልዩነት ያላቸው ዝርያዎች በመሆናቸው፣ ለምግብነት ጥቅም ላይ የሚውሉት ዓይነቴዎች በአርትሮስፒራ ስር እንዲጠቃለሉ ሆነዋል፡፡ ይሁን እንጂ ትክክለኛም ባይሆን ስፓይሩሊና የሚለው ስም ይበልጥ ታዋቂነት አለው፡፡

አርትሮስፒራ ስፓይሩሊና በመባል ለምግብነት በገበያ የዋሉ የሲያኖባክቴሪያ ዝርያዎችን ይይዛል ማለት ነው፡፡ አርትሮስፒራ ግራም ኔጌቲቭ፣ ሰማያዊ-አረንጓዴ፣ የፀሀይ ብርሃንንና ካርቦንዳይኦክሳይድን እንዲሁም ከኢ-ኢርጋኒክ ውህዶች ኤሌክትሮንን የሚጠቀሙ፣ ቀጫጭን፣ እንድና ከአንድ በላይ የተያያዙ ህዋሳት ያሏቸው፤ በብዙ ወይም በጥቂቱ ጥምዝ የሆኑ የሲያኖባክቴሪያ ዝርያ ናቸው፡፡ የተለያየ የርዝመት መጠን (ከ100-200 ማይክሮን) እና ከ8-10 ማይክሮን የሚደርስ ስፋት አላቸው፡፡

አርትሮስፒራን ከሌሎች ሲያኖባክቴሪያ የተለየ የሚያደርገው የሚኖርበት ስርዓተ ምህዳር ሲሆ ይኸውም ደቂቅ አካሉ በጣም ማእድን በበዛበት፣ ጨዋማና ሞቃት ውሃ መባዛቱ/ማደጉ ነው፡፡ ሌሎች ህይወት ያላቸው አካላት በዚህ አይነቱ ስርዓተ ምህዳር ለመኖር ይከብዳቸዋል፡፡

በዚህ ስርዓተ ምህዳር የሚኖረው አርትሮስፒራ ሌሎችን የሚያስወግድበት መንገድ፡

  • አርትሮስፒራ የሚኖርበት ስፍራ ያለውን ሶዳ ጨው(ካርቦኔትና ባይካርቦኔት) በመመገብ የውሃውን ጨዋማነት ከፍ ስለሚያደርግ (እስከ 12.5 ፒኤች ስለሚያደርሰው)
  • የአርትሮስፒራ ጥምዝምዞች ደማቅ ቀለማማና በአብዛኛው በውሃ ላይ የሚንሳፈፉ በመኖናቸውና በብቃት የፀሀይ ብርሃንን ስሚከላከሉ፣ ሌሎች ዋቅላሚዎች እንዳይኖሩ ያደርጋሉ፡፡

መቼ ታወቀ? ለማስተካከል

በመጀመሪያ የታወቀው በ1940 (እኤአ) ዴንጊርድ በተባለ ፈረንሳዊ ፋይኮሎጂስት ሲሆን ለጥናቱ መነሻ የሆነውን ናሙና ያገኘው ክሪች ከተባለና በመካከለኛው አፍሪካ በዛሬዋ ቻድ አጠገብ በነበረ በፈረንሳይ ሰራዊት ውስጥ በፋርማሲስትነት ከሚሰራ ጓደኛው ነበር፡፡ ክሪች በአካባቢው የገበያ ስፍራ በትናንሽ ብሽኩጽ መልክ የሚሸጠውን ደረቅ የባክቴሪያ ጥፍጥፍ አግኝቶ ነበር፡፡

ይሁን እንጂ ከዚህ በኋላ ስለአርትሮስፒራ ፕላተንሲስ ሳይታወቅ 25 ዓመታት ያለፈ ሲሆን እንደገናም ወደ እውቅና የመጣው ጄ.ሌዎናርድ በተባለው ቤልጄማዊ ቦታኒስት ነው፡፡

ለእውቅና መነሻ የሆነውም በቻድ ሀይቅ አካባባ ያሉት ካኔምቡዎች በየመንደሩ ባሉ የሜዳ ላይ ገበያዎች ሰማያዊ-አረንጓዴ ከኬኮችን ለሽያጭ ማቅረባቸው ነበር፡፡ የት ይገኛል? አርትሮስፒራ ፐላተንሲስ የተበለው ዓይነቴ በአፍሪካ፣ በእስያ በደቡብ አሜሪካ የሚገኝ ሲሆ አርትሮስፒራ ማክሲማ ደግሞ በመካከለኛው አሜሪካ ይገኛል፡፡

አርትሮስፒራ ፕላተንሲስ ጥልቅ ባልሆ ጨዋማ ጉድጓዶችና በሶዳ ሃይቆች የፒኤች መጠኑ ከ9-11 በሚደርስና 38.3 ግራም በሊት በሆነ በጣም ከፍተኛ ጨውነት ባለው፣ አብዛኞቹ አካላት ሲኖሩ በማይችሉበት ቦታ ተደላድሎ ይኖራል፡፡ የእሳተገሞራ አፈር አካል የሆኑት ሶድየም ካርቦኔትና ባይካርቦኔት የተባሉት ዋነኛዎቹ የጨዋማነት ማዕድኖች ናቸው፡፡

ከብርሃናዊ አስተፃምሮ አንፃር ደግሞ አርትሮስፒራ ፕላተንሲስ በሚያስደንቅ ሁኔታ ከፍተኛ የኦክሲጅን መጠን አምራች በመሆን ይታወቃል፡፡

ይጠቅማልን? ለማስተካከል

የሰው ልጅ ሰውነት የሚፈልገውን ሁሉ በተሟላ ሁኔታ ሊሰጥ የሚችል አንድም ፍራፍሬ፣ ቅጠላቅጠል ወይም የስጋ አይነት የለም፡፡ ስፓይሩሊና ግን ይህን ያሟላል፡፡ ስፓይሩሊና እስከአሁን ከታወቁት ምግቦች ይልቅ እጅግ የበለፀገ ነው፡፡

ስፓይሩሊና በ9ኛው ክፍለ ዘመን በቻድ በነበረው የካኔምብ ግዛት እንኳን ይታወቅ ነበር፡፡ ዛሬም ድረስ የደረቀና በኬክ መልክ የተዘጋጀ አልፎም በሽያጭ የሚቀርበውን “ዲሄ” የሚባለውን በየቀኑ ለምግብነት ይጠቀማሉ፡፡ ዲሄ በትናንሽ ሃይቆ ወይም ጉድጓዶች ላይ የሚንሳፈፍን የአርትሮስፒራ ፕላተንሲስ ግግር በመልምና በማድረቅ ተቆራርጦም ለሽያጭ ይቀርባል፡፡

በተመሳሳይ በ16ኛው ክፍለዘመን በሜክሲኮ ይኖሩ የነበሩ አዚቴክሶች ከቴኮኮ ሃይቅ በመልቀም ስፓይሩሊናን ለምግብነት ይጠቀሙት እንደነበር ይነገራል፡፡ ዛሬ በሚሊዮን የሚቆጠር የዓለም ህዝብ ስፓይሩሊናን ይመገባል፡፡

የሰው ልጅ ሰውነት ለመኖር ከሚያስፈልጉት ንፁህ አየርና ውሃ ባሻገር አስፈላጊ የሆኑ የንጥረ ምግብ ዓይነቶች ይፈልጋል፡፡ እነዚህ ሁሉ ደግሞ በተሟላ ሁኔታ በስፓይሩሊና ውስጥ ይገኛሉ፡፡ እነዚህ የንጥረ ምግብ ዓይነቶች ገንቢ/ጠጋኝ፣ ሀይልና ሙቀት ሰጪ፣ ቫይታሚን መዕድናት፣ ኤንዛይምና የሰውነት ቀለም ንጥሮች ናቸው፡፡

ስፓይሩሊና ያለውን የጤና ጥቅም ስናይ በቫይረስ አማካኝነት የሚመጡ በሽታዎችን፣ ካንሰርን፣ በደቂቅ አካላት አማካኝነት የሚመጡ በሽታዎችንና ሌሎች በሽታዎችን ለመከላከል ይጠቅማል፡፡ ከነዚህም ባሻገር በደም ውስጥ ያለ የስብ መጠንን፣ የስኳር በሽታን፣ የአይን፣ የደምግፊት በሽታን ለመቆጣጠርና የሰውነት ክብደትን ለመቀነስ እንዲሁም ቁስልን ለማዳን ይጠቅማል፡፡

እንዴት ጥቅም ላይ ይውላል? ለማስተካከል

 
የስፓይሩሊና እንክብል

ስፓይሩሊና በዱቄት፣ በእንክብል፣ በኬክ፣ በብስኩትና በጁስ መልክ እየተዘጋጀ ለሰው ልጅ በዋነ ምግብነትና በተጨማሪ ምግብነት ጥቅም ላይ የሚውል ነው፡፡ ከዚህም ባሻገር ለአሳ፣ ለዶሮና ለሌሎች በተጨማሪ ምግብነት ጥቅም ላይ ይውላል፡፡ የስፓይሩሊና ምርት ውዳቂም ተመራጭ የሆነውን ባዮፕላስቲክ ለማምረት ይውላል፡፡[1]

  1. ^ ስፓይሩሊና አግሮ-ኢንዱስትሪ አ/ማ ጥቅምት/2002