ስዕል ቤትደብረ ፀሐይ ቁስቋም የሚገኝ ክብ ህንጻ ሲሆን በዙሪያው አስራ ሁለት ክፍተቶች ነበሩት።

ስዕል ቤት

ሴቶች በወር አበባቸው ጊዜ ቤተክርስቲያን እንዳይገቡ መታገዳቸውን በማስመልከት እቴጌ ምንትዋብ (ብርሃን ሞገስ)፣ በየሰዓቱ (ለ12 ሰዓታት) እየሄደች ትጸልይበት ዘንድ አሰራችው። በሱዳን ደርቡሾች እስከተቃጠለ ጊዜ ድረስ፣ ህንጻው እጅግ ባማሩ ስዕሎችና ልዩ ልዩ የወርቅና የብር ጌጦች እንዲሁም በግምጃና ህብረ ቀለማዊ አልባሳት ያሸበረቀ ነበር። በዚህ ቦታ ከነበሩት ልዩ የዕደ ጥበብ ውጤቶችና አይን የሚስቡ ስዕላት አንጻር፣ ቤተ ስዕል ወይም ስዕል ቤት ተባለ። በ1879 የሱዳን ደርቡሾች አቃጠሉትና ሊፈርስ በቃ።


-1px