ስሜናዊ ቁራ ወይም ተራ ቁራ (Corvus corax) በአውርስያና በስሜን አሜሪካ የሚገኝ አዕዋፍ (ቁራ) አይነት ነው። ከብዙ ሌሎች ቁራ ዝርዮች በላይ ትልቅ ነው።

ስሜናዊ ቁራ የሚገኝበት ምድር

የወንድና የሴት ስሜናዊ ቁራ አንድ ባንድ ለሕይወት ትዳር ይቆያሉ። የቁራው ባልና ሚስት ጎጆ ይሠራሉ፣ የአካባቢያቸውን «ግዛት» ይገዛሉ። በበጋ ወራት ሴት ስሜናዊ ቁራ 3-7 እንቁላል ትጥላለች። ወጣቶቹም አብረው ይጓዛሉ፤ ለሬሳዎችም ሆነ ለቆሻሻ ለመብላት ይወዳደራሉ።

ይህ ዝርያ ከአዕዋፍ ሁሉ የአዕምሮ ብልሃት እንዳለው ይታመናል። ስላገኙት ነገሮች በጩኸታቸው እርስ በርስ ማወራት ይችላሉ። ጨዋታ ሲጫወቱም ታይተዋል። የቁራ ወጣት ስለ አዳዲስ፣ ብሩኅ እቃዎች ትልቅ ጉጉት አለው። ታድጎ ሲያርጅ ግን የቁራ ዓዋቂ አዳዲስ ነገሮችን ምንም አይወድድም።