ሳንክት ፔቴርቡርግ (Санкт-Петербург) የሩስያ ከተማ ነው። 4.9 ሚሊዮን ኗሪዎች አሉት። በሩስያ ንጉሥ ጻር 1 ፔቴር1695 ዓ.ም. በሞስኮ ፈንታ የሩስያ ዋና ከተማ እንዲሆን ተመሠረተ። ከዚያ እስከ 1910 ዓ.ም. የሩስያ ዋና ከተማ ነበረ። በ1906 ዓ.ም. ስሙ ከሳንክት ፔቴርቡርግ ወደ ፔትሮግራድ ተቀየረ። በ1910 ዓ.ም. ዋና ከተማው ወደ ሞስኮ ተመለሰ። በ1916 ዓ.ም. ስሙ እንደገና ከፔትሮግራድ ወደ ሌኒንግራድ ተቀየረ። በ1983 ዓ.ም. ግን ስሙ ወደ ሳንክት ፔቴርቡርግ ተመለሰ።

Coat of Arms of Saint Petersburg (2003).svg