ሳምባ
ሳምብ በአብዛኛ የጀርባ አጥንት ባላቸው እንስሳት ዘንድ የሚገኝ ብልት ነው። ዋና ተግባሩም ከውጭው አለም ያልተቃጠለ አየር (ኦክሲጅን)ን ወስዶ በ ደም ላይ በመጫን ወደ ልብ መላክና ከልብ የተቃጠለ አየር (ካርቦን ዳይኦክሳይድ) ተጭኖ የሚመጣን ደም የተጫነውን የተቃጠለ አየር አውርዶ ወደውጭ መተንፈስ ነው። የጀርባ አጥንት ካላቸው እንስሳቶች አብዛኞቹ 2 ሳምባዎች አሏቸው።
የሰው ልጅ ሳምባ አብዛኛው ክፍሉ በቱቦዎች እና በሚሊዮኖች በሚቆጠሩ ጥቃቅን ስልቻዎች የተሞላ ነው። እኒህ የአየር ጥቃቅን ስልቻዎች አሊቮሊ ይሰኛሉ።