ሲ (የኮምፒዩተር ፍርገማ ቋንቋ)
ሲ የኮምፑተር ፍርገማ ቋንቋ (የተለመደ አጠራሩ ሲ) ለሲፊ አላማ የሚውል የተደራጀ ትዕዛዝ ተኮር የኮምፒውትር ፍርገማ ቋንቋ ሲሆን ለዪኒክስ የሲስተም አሰሪ ተብሎ በ1970ዎቹ መጀመሪያ ላይ በደኒስ ሪቺ ተሰርቶ ቀረበ። ከዚያ ወዲህ በአብዛኛው የኮምፒዩተር የሲስተም አሰሪ ተስፋፍቶ በአለም በስፋት ከሚያገለግሉ የፍርገማ ቋንቋዎች አንዱ ነው። ሲ ሌሎች ታዋቂ የፍርገማ ቋንቋዎች ገጽታ ላይ ታላቅ ሚና ተጫውቶዋል። በተለይም ሲ++ ለሲ ማሻሻያ ተብሎ የታቀደ ቋንቋ ነው። የተመጠነና ብቃት ያለው ኮድ ለማውጣት የተመቻቸ ቋንቋ ሆኖ ሲታወቅ፣ የሲስተም አሰሪ ሶፍትዌሮችን ለመስራት የተለመደ ቋንቋ ሆኖ ሳለ ሌሎች ሶፍትዌሮችንም ለመጻፍ በስፋት ያገለግላል።