ስዋሰው sewasew.com በ[[አማርኛ]]፣ [[ትግርኛ]]፣ [[ኦሮምኛ]]ና [[እንግሊዝኛ]] የሚጻፍ የሥነ እውቀት ድረ ገጽ ነው። አላማው ስለ አፍሪካ ማንኛውም መረጃ ለማቅረብ ሲሆን፣ ማንም ሰው በኢንተርኔት በኩል አባል ሊሆንና መሳተፍ ይችላል።

ማንም ሰው በኢንተርኔት ሊሳተፍ ስለሚችል በዚህ ረገድ እንደ ውክፔዲያ ይመስላል፤ የቀረቡት መጣጥፎችና መረጆች ግን በዊኪ መሻሻያ መርሃግብር ውስጥ ሳይሆኑ፣ በተለመደው ጥያቄና መልስ ብሎግ ፎርማት ነው። የመስራች ሶፍትዌር ባለሙያዎች እንደ ገለጹ፦

«የሰዋስው አባላት ህልም ማንኛውም ሰው በቀላሉ ሊያገኘው እና በራሱ ቋንቋ ሊጠቀመው የሚችል መድረክ መፍጠር ነው። የሰዋስው አባላት ህልም፣ አጠቃቀሙ ቀላል የሆነ እና ከተለያዩ መገልገያዎች ላይ በቀላሉ መጠቀም የሚችሉት መገልገያ መስራት ነው። በመጨረሻም፣ ሰዋስው አድጎ እና ተመንድጎ ማንኛውም አፍሪካዊ የሆነ መረጃ መገኛ ቦታ እንዲሆን ነው።»

የውጭ መያያዣ

ለማስተካከል