ራባት
ራባት (الرباط /ሪባጥ/) የሞሮኮ ዋና ከተማ ነው።
የሚኖርበት የህዝብ ቁጥር 1,636,600 ሆኖ ይገመታል። ከተማው 34°01′ ሰሜን ኬክሮስ እና 6°50′ ምዕራብ ኬንትሮስ ላይ ተቀምጦ ይገኛል።
ሥፍራው መጀመርያው የተሠፈረ በ3ኛ ክፍለ ዘመን ክ.በ. ሲሆን ስሙ ቸላ ተባለ። በ32 ዓ.ም. ሮማውያን ያዙትና ስሙን ሳላ አሉት። ሮማውያን እስከ 242 ዓ.ም. ድረስ ከተማውን ይዘው የዛኔ ለበርበር ሕዝብ ግዛት ተመለሠ። በ1162 ዓ.ም. ሪባጥ (ራባት) ተብሎ ተሰየመ። በ1187 ዓ.ም. የአልሞሃድ መንግሥት ዋና መቀመጫ ሆነ።
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |