ሥነ ስብስብ
ሥነ ስብስብ የሒሳብ ቅርንጫፍ ሲሆን ትኩረት ሰጥቶ የሚያጠናው ስብስቦችን ነው። ስብስብ ማለቱ ተለይተው ሊታወቁ የሚችሉ ነገሮችን ክምችት ወይም ቡድን ነው።
የሥነ ስብስብ ኅልዮት በጣም መሰረታዊ ከመሆኑ የተነሳ ማናቸውንም የሒሳብ ቅርንጫፎች በርሱ ቋንቋ መጻፍና መተርጎም ይቻላል። ከቀላልነቱም አንጻር በመዋዕለ ሕጻናትና በአንደኛ ደረጃ ትምህርትቤቶች ደረጃ ሳይቀር ለህጻናት ቢቀርብ ምንም ጉዳት አያመጣም። የስብስብ ውህደትና የጋራ መተግበሪያወች እንዲሁም ቬን ዲያግራምና ኦይለር ዳያግራም በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ሊሰጡ ይችላሉ፣ ከበድ ያሉት እንደ ተቆጣሪነት አይነት ጽንሰ ሃሳቦች በኮሌጅ ደረጃ ይቀርባሉ።
ሥነ ስብስብ የተመሰረተው በ1860ወቹ በጆርጅ ካንተር እና ሪቻርድ ደደኪንድ በተሰኙ የሂሳብ ተማሪወች ነበር። እኒህ ተመራማሪወች፣ በተለይ ካንተር፣ የዋህ ሥነ ስብስብ ተብሎ አሁን የሚታወቀውን ጥናት መሰረት ቢጥልም በ20ኛ ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ በበርትራንድ ረስልና ሌሎችም ተማሪወች የዚህ አዲሱ የሂስብ ዘርፍ ኃልዮት ለርስ በርስ ቅራኔ እንደሚያበቃ በማስረዳታቸው ዘርፉ ሊሻሻል በቃ። ይህ አዲሱ የሥነ ስብስብ ስርዓት እሙናዊ የስብስብ ኅልዮት በመባል ይታወቃል።
ደግሞ ይዩ፦
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |