ሰው ሰራሽ እውቀት አሳቢ የሆኑ ማሽኖች እና ሶፍትዌር የሚሰሩበት እና የሚጠኑበት ዘርፍ ነው። የዘርፉ ዋና ዋና ተመራማሪዎች እና መፅሃፍት ዘርፉን ሲገልፁ "አሳቢ ነገሮችን የሚሰራ እንዲሁም የሚያጠና" ብለው ነው። አሳቢ ወይም አዋቂ ነገር የሚለው አገላልፅ የሚያመለክተው ስላሉበት አካባቢ ለመረዳት መቻልን እና ከዚሁ መረዳት በመነሳት (ለመኖር የሚያስችል) ተመጣጣኝ ድርጊት ለማድረግ መቻልን ነው። ይህን ስያሜ ለመጀመሪያ ጊዜ በ 1955 የተጠቀመበት ጆን ማካርቲ ዘርፉን ሲገልፅ "አሳቢ ወይም አዋቂ ማሽኖችን ለመስራት የሚደረግ ሳይንስምህንድስና" ይለዋል።

ዘርፉ ባጠቃላይ የረቀቀና እና ገና ሁሉ አቀፍ ያልሆነ (ስፔሻላይዝድ) ነው። በዘርፉ ያሉት ልዩ ልዩ የጥናትና የምርምር ክፍሎችም የተከፋፈሉና እርስ በርስ ግንኙነት የማያደርጉ ናቸው። ከክፍፍሉ ምክንያቶች ውስጥ ታሪካዊና ማህበራዊ ምክንያቶሽ ይጠቀሳሉ ማለትም የተለያዩ የጥናትና የምርምር ክፍሎች ያደጉት በተለይ ዘርፉን በመሰረቱ ድርጅቶችና በግለሰቦች ጥረት መሆኑ ናቸው።