ሞንዞን (እስፓንኛ፦ Monzón) በእስፓንያ የሚገኝ መንደር ነው።

ሞንዞን
Monzón
የሞንዞን አምባ
ክፍላገር አራጎን
ከፍታ 273 ሜ.
የሕዝብ ብዛት
   • አጠቃላይ 17,115
ሞንዞን is located in እስፓንያ
{{{alt}}}
ሞንዞን

41°54′ ሰሜን ኬክሮስ እና 0°11′ ምሥራቅ ኬንትሮስ

አምባው በእስልምና ግዛት በ8ኛው ክፍለ ዘመን ዓ.ም. ተሠራ። ክርስቲያኖች በ1075 ዓ.ም. መለሱት። ከ1081 እስከ 1135 ዓ.ም. ድረስ ራስ-ገዥ የሞንዞን መንግሥት ዋና ከተማ ነበር። እስላሞች ግን ከ1118 እስከ 1122 እና ከ1128 እስከ 1133 ዓ.ም. ድረስ እንደገና ያዙት። በ1135 ዓ.ም. ከተማው ለቴምፕላርስ ተሸጠ። ከዚያ በኋላ የአራጎን መንግሥት ግቢ፣ ችሎት ወይም ፓርላማ አንዳንዴ በሞንዞን ይገኝ ነበር።