ምልምሎች

(26) ለእንጦጦ ማርያም ይመስለኛል ጣይቱ ለመዘምራንነት ድምጸ መረዋ የሆኑ ስልቦችን ለአገልጋይነት ይሰጣሉ። እነዚህ መዘምራን ከአለቃ ጋር በምን እንደተጣሉ አይታወቅም። አለቃ እነሱን እናንተ ምልምሎች ይሏቸዋል። መዘምራኑም ምኒልክ ዘንድ ይከሳሉ ተሰደብን ብለው። አለቃም ተጠርተው ሲጠየቁ አልተሳደብኩም ይላሉ። ከዚያ ምን ብሎ ነው አለቃ የሰደባችሁ ይላሉ ምኒልክ። መዘምራኑ አፍረው ዝም ሲሉ አለቃ ምን ትላለህ ይሏቸዋል። አለቃም አልተሳደብኩም እቴጌ ጣይቱ ከአገልጋዮቻቸው መካከል መርጠው መልምለው ለእንጦጦ ማርያም ስለሰጡ ነው ምልምሎች ያልኩት አሉ። ምኒልክም ስቀው ዝም አሉ አሉ።