ማዖሪ ቋንቋ (Māori ወይም Te Reo Māori /ቴ ሬዖ ማዖሪ/፣ በአጭሩ Te Reo «ቋንቋው») ከኒው ዚላንድ መደበኛ ቋንቋዎች አንዱ ነው። የምሥራቅ ፖሊኔዚያ ደሴቶች ቋንቋ ቤተሠብ አባል ሲሆን የታሂቲ እና የሃዋይኢ እንዲሁም የሳሞዓ እና የቶንጋ ቋንቋዎች ዘመድ ነው። የተናጋሪዎቹ ቁጥር 100,000 የሚያሕል ነው።

ይፋዊ ኹኔታEdit

ኒው ዚላንድ አሁን ሦስት መደበኛ ቋንቋዎች ያሉት ማዖሪ፣ እንግሊዝኛና የኒው ዚላንድ እጅ ቋንቋ ናቸው። ስለዚህ አብዛኛው የመንግሥት ዘርፎች ሁለት ስሞች አላቸው፤ ለምሳሌ የውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር Department of Internal Affairs (/ዴፓርትሜንት ኦቭ ኢንተርናል አፈይርዝ/) በእንግሊዝኛ፣ ደግሞም Te Tari Taiwhenua (/ቴ ታሪ ታይፌኑዋ/) በማዖሪ ተብሎ ይታወቃል። ከመጋቢት 1996 ዓ.ም. ጀምሮ የማዖሪ ቴሌቪዥን አገልግሎት በመንግስት እርዳታ ኖሯል።

ታሪክEdit

ማዖሪ ወደ ኒውዚላንድ ያመጡት ፖሊኔዝያውያን ሰዎች ከሌሎች ደሴቶች የደረሱ ምናልባት በታንኳ ነበር። ከ1860ዎቹ በኋላ ግን እንግሊዞች በኒው ዚላንድ በሠፈሩበት ጊዜ እንግሊዝኛ አመጡና ትምርት ቤቶች ሲከፈቱ ከ1880ዎቹ የማዖሪ ጥቅም በትምህርት ቤት ውስጥ ተከለከለ። በዚህ ብዙዎች የማዖሪ ሕዝብ እንግሊዝኛ በግዴታ ተማሩ። ነገር ግን እቤት ውስጥ፥ በአምልኮት፥ በፖለቲካ ስብሰባ ወዘተ. የማዖሪ ቋንቋ መናገሩ ፈጽሞ አልተቋረጠም። ከዚያ በላይ አንዳንድ የማዖሪ ጋዜጣም ሆነ መጽሐፍ ይታተም ነበር። በ1980ዎቹ 20 ከመቶ ማዖሪዎች ብቻ እንደ ኗሪ ቋንቋ ይችሉት ነበር። በዚያን ጊዜ ቋንቋው ለዘለቄታ እንዳይጠፋ አዲስ የማዖሪ ቋንቋ እንቅስቃሴ ተጀመረና የማዖሪ ትምህርት ቤቶች ተከፈቱ።

ፊደልEdit

ማዖሪ የሚጻፍበት በላቲን ጽሕፈት አይነት አልፋቤት ሲሆን ፊደሎች እንዲህ 20 ናቸው፦

A Ā E Ē H I Ī K M N O Ō P R T U Ū W NG እና WH

ሁላቸው እንደ ተለመደ ድምጾች አላቸው 'WH' የሚያሰማው ድምጽ ግን እንደ 'ፍ' ይመስላል።

ቁጥርEdit

የአብዛኛው ስሞች ቁጥር የሚታይበት ዘዴ የተወሰነ መስተጻምር በመለወጡ ነው። ለነጠላ ቁጥር መስተጻምሩ te 'ቴ' ሲሆን ለብዙ ቁጥር nga 'ንጋ' ይሆናል። ስለዚህ፦

ika (ኢካ) - ዓሣ፤ rākau (ራካው) - ዛፍ
te ika (ቴ ኢካ) - ዓሣው፤ te rākau (ቴ ራካው) - ዛፉ
ngā ika (ንጋ ኢካ) - ዓሦቹ፤ ngā rākau (ንጋ ራካው) - ዛፎቹ

ሰላምቶችEdit

  • Kia ora ኪያ ዖራ - ሰላምታ፤ እግዜር ይስጥልኝ
  • Hei konei ኸይ ኮነይ - ደህና ዋል / ዋይ
  • Kei te pēhea koe ከይ ቴ ፔኸያ ኮዌ - እንደምን ነህ / ነሽ?
  • Kei te (tino) pai ahau ከይ ቴ (ቲኖ) ፓይ አሃው - እኔ (በጣም) ደህና ነኝ

External linksEdit

ReferencesEdit

  • Biggs, Bruce (1994). Does Maori have a closest relative? In Sutton (Ed.)(1994), pp. 96–-105.
  • Biggs, Bruce (1998). Let's Learn Maori. Auckland: Auckland University Press.
  • Clark, Ross (1994). Moriori and Maori: The Linguistic Evidence. In Sutton (Ed.)(1994), pp. 123–-135.
  • Harlow, Ray (1994). Maori Dialectology and the Settlement of New Zealand. In Sutton (Ed.)(1994), pp. 106–-122.
  • Sutton, Douglas G. (Ed.) (1994), The Origins of the First New Zealanders. Auckland: Auckland University Press.