ማከዶን (ግሪክኛ፦ Μακεδών) ወይም ማከድኖስ (ግሪክ፦ Μακεδνός) በጥንታዊ ግሪክ አፈ ታሪክ የመቄዶን አገር መሥራች። ይህ አገር ቀድሞ ኤማጥያ ይባል ነበር።

ጸሐፊው ዲዮዶሮስ ሲኩሉስ እንደሚለን፣ ማከዶንና አኑቢስኦሲሪስ አፒስ ልጆች ነበሩ፤ ከኦሲሪስ ጋር ወደ አገሮች ሁሉ፣ በአፍሪቃ እስያአውሮፓ ይጓዙ ነበር። አኑቢስ የውሻ ቆዳ እንደ ካባ ይለብስ ነበር፤ ማከዶንም የተኲላ ፍርምባ ለበሰ። በኋላ ኦሲሪስ ልጁን ማከዶን በመቄዶን አገር ላይ እንደ ንጉሥ ለቀቀው።

በሌሎች ምንጮች ማከዶን ወይም ማከድኖስ ከዚውስጡያ (የዲውካልዮን ሤት ልጅ) ተወለደ። በልዩ ልዩ ተቃራኒ ምንጮች ደግሞ የማከዶን አባት አዮሉስሉካዎን፣ ወይም አያኮስ ይባላል።