ማከዶን
(ከማከድኖስ የተዛወረ)
ማከዶን (ግሪክኛ፦ Μακεδών) ወይም ማከድኖስ (ግሪክ፦ Μακεδνός) በጥንታዊ ግሪክ አፈ ታሪክ የመቄዶን አገር መሥራች። ይህ አገር ቀድሞ ኤማጥያ ይባል ነበር።
ጸሐፊው ዲዮዶሮስ ሲኩሉስ እንደሚለን፣ ማከዶንና አኑቢስ የኦሲሪስ አፒስ ልጆች ነበሩ፤ ከኦሲሪስ ጋር ወደ አገሮች ሁሉ፣ በአፍሪቃ እስያና አውሮፓ ይጓዙ ነበር። አኑቢስ የውሻ ቆዳ እንደ ካባ ይለብስ ነበር፤ ማከዶንም የተኲላ ፍርምባ ለበሰ። በኋላ ኦሲሪስ ልጁን ማከዶን በመቄዶን አገር ላይ እንደ ንጉሥ ለቀቀው።
በሌሎች ምንጮች ማከዶን ወይም ማከድኖስ ከዚውስና ጡያ (የዲውካልዮን ሤት ልጅ) ተወለደ። በልዩ ልዩ ተቃራኒ ምንጮች ደግሞ የማከዶን አባት አዮሉስ፣ ሉካዎን፣ ወይም አያኮስ ይባላል።
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |