ማርሲ (ማርሳውያን) በራይንሊፐ ወንዞች መካከል የሠፈረ አነስተኛ ጀርመናዊ ጎሣ ነበሩ። ምናልባት የሱጋምብሪ ነገድ ከዚያ ዙሪያ ከተሰደዱ በኋላ የቀሩት ሕዝቦች ይሆናሉ።[1] ስትራቦን እንደ ገለጸው ማርሲ መጀመርያ ከራይን አካካቢ ቢሆኑም አሁን በሮሜ መንግሥት ጦርነት ምክንያት ወደ ጌርማኒያ ውስጥ ፈለሱ።[2]

የማርሲ ሥፍራ ከጌርማኒያ ነገዶች መካከል በሮሜ መንግሥት ዘመን

ታኪቱስ በተለይም የጌርማኒኩስ ዘመቻዎች ሲተርክ ብዙ ጊዜ ማርሳውያንንና አለቃቸውን ማሎወንዱስ ይጠቅሳቸዋል። በ1 ዓ.ም. የቸሩስኪ ብሔር ጦር አለቃ አርሚኒዩስ ሦስቱን የሮሜ ሥራዊት ባጠፋቸው በቴውቶቡርግ ደን ውግያ ሰዓት፣ ማርሲ ደግሞ ከርሱ ጋር ተባብረው ነበር። የሮሜ አለቃ ገርማኒኩስ ቂሙን ለመብቀል ሲል በ6 ዓ.ም. ከታላቅ ሥራዊት ጋር የማርሲ ምድርን ወረረ። በዚያን ጊዜ ማርሳውያን የአረመኔ ጣኦታቸውን የታንፋና በዓል እየከበሩ ስለ ሆነ፣ ማርሳውያን ሰክረው በድንገት ተያዙና በፍጹም ተገደሉ። ታኪቱስ እንደሚለው (Annals 1, 51)፣ ሰፊ አውራጃ (፶ የሮሜ ማይል ዙሪያ) በእሳትና በሠይፍ ተዘረፈ፣ «ማንም ጾታ ወይም ዕድሜ ምኅረት አላገኘም» ይለናል።

ተመሳሳይ ዕልቂት በ7 ዓ.ም. በካቲ ጎሣ ላይ ተደርጎ የተረፉት ጀርመናዊ ነገዶች እንደገና ተባበሩና በ9 ዓ.ም. ሮማውያን እስከ ቬዘር ወንዝ ድረስ ለመግዛት ያሠቡትን ዕቅድ ተዉ፣ ለዘለቄታም ወደ ራይን ማዶ ተመለሡ።

አሁን የአንዳንድ መንደር ስም የጥንታዊ ማርሲ ትዝታ ይከብራል፦ ለምሳሌ ማርስበርግ እና ፎልክማርዘን

ዋቢ ምንጮች

ለማስተካከል
  • Beatrix Günnewig, Günter Neumann: Marsen. In: Reallexikon der Germanischen Altertumskunde. Bd. 19. Berlin 2001, S. 361ff. (ጀርመንኛ)
  • Ralf G. Jahn: Der Römisch–Germanische Krieg (9-16 n. Chr.). Dissertation University Bonn 2001. (ጀርመንኛ)