መፈንቅል የማይልመጠመጥ ጠንካራ እቃ ሲሆን ከደጋፊ ችካል ላይ በመቀመጥ ሸክምን ለማንሳት በሚደረገው ስራ ጉልበትን ለማባዛት ወይም ሸክሙ የሚሄደውን ርቀት ከፍል ለማድረግ የሚጠቅም ቀላል ማሽን ነው። የጥንቱ የግሪክ ሂሳብ ተመራማሪ የነበረው አርክሜድስ፣ የመፈንቅልን ጉልበት የማብዛት ጠባይ በማዳነቅ እንዲህ ብሎ ነበር የምቆምበት ቦታ ስጡኝ እንጂ፣ መሬትን በመፈንቅል አነሳታለሁ። በጥንቱ ግብጽ አናጺወች ወደ 100 ቶን የሚጠጉ የድንጋይ ቅርጾችን በመፈንቅል ያነሱ እንደነበር ታሪክ ይዘግባል [1]

መፈንቅል

የመፈንቅል አይነቶች

ለማስተካከል
  • ዓይነት 1፡ መደገፊያው በጉልበቱና በሸክሙ መካከል የሆነ። ምሳሌ መቀስከፍ-ዝቅ
  • ዓይነት 2፡ ሸክሙ በመደገፊያውና በጉልበቱ መካከል የሆነ። ምሳሌ እጅ ጋሪ
  • ዓይነት 3፡ ጉልበቱ በሸክሙና በመደገፊያው መካከል የሆነ። ምሳሌ ትዊዘርየሰው ልጅ መንጋጭላ
  1. ^ Budge|first=E.A. Wallis|title=Cleopatra's Needles and Other Egyptian Obelisks‎|publisher=Kessinger Publishing|year=2003|page=28|isbn=9780766135246

ተጨማሪ ንባቦች

ለማስተካከል