መለጠፊያ:የለቱ የኢትዮጵያ ተፈጥሮ ነክ ምርጥ ጽሑፍ

ጌሾ


ጌሾ

ጌሾአፍሪካ ብቻ የሚበቅል በተለይ በኢትዮጵያና በደቡብ አፍሪካ የሚገኝ ተክል ነው። በኢትዮጵያ ጠላና ለጠጅ ሲጠመቅ ጌሻ ይገባል። የሚበቅለውም ከባህር ወለል በላይ 1400-3200 ሜትር ላይ ነው።

መድሃኒታዊ ጥቅም

ለማስተካከል

-ቆረቆርና ሌሎች የፈንገስ በሽታወችን በደቀቀ ፍሬውና ቅጠሉ በመቀባት ለማዳን ይቻላል - ህጻናት እንጥላቸው ከተቆረጠ በኋላ ህመማቸውን ለማስታገስ አፋቸው ውስጥ የጌሾ ቅጠል ይደረጋል -ቂጥኝ በሽታን ለመከላከል -ሆድ ድርቀት ለማስወገድ - ሥሩ ደምን ለማጥራት ያገለግላል

ሌሎች ጥቅሞች

ለማስተካከል

የጌሾ ግንድ በጣም ጠንካራ ስለሆነ ለተለያዩ የእንጨት ውጤቶች ሊያገለግል ይችላል። የጌሾ ዛፍ በምንጮች አካባቢ ቢተከል የመሬት መሸርሸርን ሊከላከል ይችላል። ከእርሻ ማሳ ዳርቻ ላይ በመትከልም የመሬትን ንጥር ነገር ከነፋስ እና ከዝናብ መከላከል ይቻላል። የጌሾ አበቦች በንቦች ዘንድ ከፍተኛ ተወዳጅነት ስላላቸው የጌሾ ተክል ለንብ እርባታና ለማር ምርት ከፍተኛ ግልጋሎት ሊሰጥ ይችላል።

....