የ “እስልምና እና የታላቁ ነቢይ የሙሐመድ ታሪክ[1] መጽሃፍ ደራሲ ናቸዉ።

ሐጂ ሙሐመድ ሣኒ ከዚያች መጽሐፍ በፊት (በ1963) ከሼኽ ሰይድ ሙሐመድ ሳዲቅ ጋር በመሆን ቅዱስ ቁርኣንን ወደ አማርኛ ተርጉመዋል።

ሓጂ ሙሐመድ ሣኒ ሐቢብ

ሓጂ ሙሐመድ ሣኒ ሐቢብ የሚጠቀሱበት ሌላው ታሪክ የኢትዮጵያው መጅሊስ እንዲመሰረት ያደረጉት ተጋድሎ ነበር። በንጉሡ ዘመን መጅሊስ የሚባል ነገር አይታወቅም(“መጅሊስ” ይቅርና ዐረፋና ዒድ አልፈጥርም አይከበሩም ነበር)። በመሆኑም የኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞችን መብትና ጥቅም በጋራ የሚያስከብር ተቋም አልነበረም። ሙስሊሞችን ወክሎ የሚናገር፣ የሃጂና ዑምራ ጉዞአቸውን የሚያቀላጥፍ፣ መስጂዶችንና አውቃፍን የሚገነባና የሚያስተዳድር ተቋም ያስፈልግ ነበር። ሓጂ ሙሐመድ ሣኒ ከሌሎች ዑለማ ጋር በመሆን ሙስሊሞች የራሳቸው ተቋም እንዲኖራቸው ለረጅም ጊዜ ይሟገቱ ነበር። የ1966ቱ አብዮት ሲፈነዳ ህዝበ ሙስሊሙ መብቱ እንዲከበርለት የሚጠይቀውን የሚያዚያ 20/1966 ታላቅ ህዝባዊ ሰልፍ አደረገ። ሓጂ ሙሐመድ ሳኒ ሐቢብም የመጅሊሱን ጉዳይ ይዘው ከመንግሥት ጋር መሟገታቸውን ቀጠሉ። በአላህ ፈቃድ ትግሉ ሰምሮ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በብሄራዊ ደረጃ ተቋቋመ። ሓጂ ሙሐመድ ሣኒም ይህንን ተቋም እስከ እለተ ሞታቸው ከመሩት በኋላ በ1981 አረፉ። አላህ ስራቸውን ይውደድላቸው። [2]