መጽሐፈ ሲራክ ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከእየሱስ ክርስቶስ መወለድ ሁለት መቶ አመት ቀደም ብሎ በእብራይስጥ ልሳን በሰምዖን ቤን ኤልኤዜር ቤን ሲራክ የተፃፈ ሲሆን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተከርስቲያን ዘንድም መጽሐፉ ከመፅሀፍ ቅዱስ ከብሉይ ኪዳን መጻሕፍት የሚፈረጅ ነው። ለማንበብ እታች ይጫኑ።

«እግዚአብሔር መድኃኒትን ከምድር ፈጥሯልና አዋቂ ሰው ባለ መድኃኒትን አይንቀውም። ታምራቱን ያወቁ ዘንድ ውሃ በእንጨት የጣፈጠ አይደለምን? በታምራቱ ይከበሩ ዘንድ እግዚአብሔር ለሰዎች ጥበብን ሰጣቸው። በመድኃኒቱ ያድናቸዋል በሽታቸውንም ያርቅላቸዋል። በሚያድኑ ገንዘብ ከነሳቸው መድኃኒት ያደርጋሉ እሱም ለሀገር ፍቅርን ያመጣል።» ፴፰፡፬-፰።

እግዚአብሐር ፈጠረ ሥራያተ እምነ ምድር ወብእሲሰ ጠቢብ ኢይሜንኖ። አኮኑ ብዕፅ ጥዕመ ማይ ከመ ያእምሩ ኅይሎ። ወውእቱ ወሀቦሙ ለእጓለ እምሕያው ጥበበ፤ ከመ ይከበሩ በሰብሐቲሁ። ወቦቱ ይፌውሶሙ ወያሴስል ኲሎ ሕማሞሙ። እምውስቴቱ ይገብሩ ሥራያተ በዘ ይፌውሱ ወውእቱ ያመጽእ ስላመ ለብሔር።

የሚያዩት ገጽ ላይ ወይም እዚህ ላይ [1] በመጫን የመጽሐፉን ገጾች ማንበብ ይችላላሉ