ከ«ትምህርተ፡ጤና» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
መስመር፡ 1፦
==''' የህብረተሰብ ጤና '''==
 
የአለም ጤና ጥበቃ ድርጅት ጤንነትን እንደሚከተለው ይተነትነዋል፡፡ ጤንነት ማለት ሙሉ የሆነ የአካል፡ የስነልቦናዊ፡የ[[የሥነ፡ልቡና ትምህርት|ስነልቦናዊ]]፡ እንዲሁም የማህበረሰብአዊ ደህንነት ነው፡፡ ይህም ሲባል የበሽታ አለመኖር ብቻ ጤነኝነትን አይገልፅም፡፡ http://www.who.int/about/definition/en/
 
ስለዚህም በሽታ ማለት የማንኛውንም ግለሰብ የአካል፡ የስነልቦናዊ፡ ወይም የማህበረሰብአዊ ደህንነትን የሚያቃውስ ሁኔታ ነው፡፡
መስመር፡ 7፦
 
በሽታ በተለያየ ጠንቅ መንገድ ሊነሳ ይችላል፡፡
*1. በተፈጥሮ የሚከሰት አካላዊ/ ይዘታዊ ጉድለት ወይም መዛባት (ለምሳሌ፡ ሴት የአንጀት ማውጫ ቀዳዳ ወይም ፊንጢጣ አለመበሳት))
*2. በዘር የሚወረስ ለተወሰኑ በሽታዎች ተጠቂነት (ለምሳሌ፡ የደም አለመርጋት ችግሮች)
*3. ከወሊድ ችግሮች ጋር በተያያዘ (ለምሳሌ፡ የነርቭ ጉዳት)
*4. በጥቃቅን ህዋሳት ምክንያት
**a. ቫይረሶች፡ (ለምሳሌ፡ኩፍኝ፤ጉድፍ፤ጆሮ ደግፍ፤ ጉንፋን፤የህፃናት ተቅማጥ፤
**b. ባክቴሪያዎች (ለምሳሌ፡ የሳምባ ምች፤ተስቦ፤የደም ተቅማጥ፤ የሳምባ ነቀርሳ፤
**c. ጥገኞች፤ ፓራሳይቶች (ለምሳሌ፡ ግርሻ፤ ወባ፤ሻህኝ፤ እንዲሁም ዝሆኔ፤ የውሻ ኮሶ፤ ወስፋት እና ሌሎች ጥገኛ የአንጀት ትላትሎች)
**d. ፈንገሶች (ለምሳሌ ጭርት እና መሰል የቆዳ በሽታዎች)
*5. በምግብ ወይም አስፈላጊ የምግብ ንጥረ ነገሮች ጉድለት (ለምሳሌ፡ የደም ማነስ፤ ክዋሾርኮር)
*6. በአካል ላይ በሚደርስ ቀጥተኛ አደጋ፡ (ለምሳሌ፡ ቃጠሎ፡ የመኪና አደጋ፡ ድብደባ)
መስመር፡ 23፦
 
===ተላላፊ በሽታዎች===
በ[[አፍሪካ]] እና በሌሎችም ታዳጊ ሀገሮች ውስጥ አብዛኛውን ህብረተሰብ የሚያጠቁት በሽታዎች በጥቃቅን ህዋሳት አማካኝነት የሚተላለፉ እና በምግብ እጥረት ምክንያት የሚመጡት ናቸው፡፡ የአለም ጤና ጥበቃ ድርጅት የ2004 ዓምዓ.ም. መረጃ እንደሚያሳየው በተለይም ወባ፡ የሳምባ ነቀርሳ፡ ኤድስ እንዲሁም የህጻናት ጠቅማጥ እና የሳማባ ምች ለብዙ የምርት እና የትምህርት ሰዐታት መባከን ምክንያት ናቸው፤ እንዲሁም በየአመቱ ብዙ ህይወት ይቀጥፋሉ፡፡
 
በህዋሳት ምክንያት የሚመጡት በሽታዎች እንደ ህዋሳቱ እይነት የተለያየ የመተላለፊያ መንገድ ያላቸው ሲሆን ባጠቃላይ ግን እኒህ መተላለፊያ መንገዶች እንደሚከተለው ይመደባሉ፡
*1. በምግብ የሚተላለፉ፡-(ለምሳሌ ኮሶ፤ የምግብ መመረዝ፤ተስቦ፤የህፃናትመመረዝ፤ ተስቦ፤ የህፃናት ተቅማጥ )
*2. ውሃ ወለድ፡ (ለምሳሌ ኮሌራ፡ ተስቦ፤ )
*3. ከሰገራ ጋር በሚኖር ንክኪ (ማለትም በእጅ፡ በዝንቦች ወይም ከመጠጥና ምግብ ጋር በሚኖር ንክኪ) የሚተላለፉ (ለምሳሌ ወስፋት፤ አሜባ፤ የህፃናት ተቅማጥ)
*4. በነፍሳት (የተለያዩ ትንኞች/ መዥገር/ ቅማል) የሚተላለፉ (ለምሳሌ ወባ፡ ቢጫ ወባ፤ሻህኝ፤ወባ፤ ሻህኝ፤ ግርሻ)
*5. በቀጥተኛ ንክኪ የሚተላለፉ (ለምሳሌ፡ የቁስል ማመርቀዝ፡ የአይን ማዝ፤ የተለያዩ የቆዳ በሽታዎች፤ የእብድ ውሻ በሽታ)
*6. በወሲብ የሚተላለፉ (ለምሳሌ ኤድስ፤ ቂጥኝ)
መስመር፡ 35፦
*8. በትንፋሽ/ በአየር የሚተላለፉ (ለምሳሌ ማጅራት ገትር፤ ኩፍኝ፤ ጉድፍ፤ ጉንፋን፤ የሳምባ ነቀርሳ)
 
ከበሽተኛው አገላለፅ እና የአካል ምርመራ በተጨማሪ አንድን በሽታ በተላላፊ ህዋሳት ነው የሚመጣው ለማለት የሚያበቁ መረጃዎች ያስፈልጋሉ፤ እነዚህም መረጃዎች የተላላፊው ህዋስ ወይንም ሰውነታችን ህዋሱን በተለይ ለመከላከል የሚያመነጨው የተለየ ፀረ-ህዋስ ኬሚካል በበሽተኛው ሰውነት ውስጥ መገኘትን ያጠቃልላል፡፡ በዚህም ምክንያት በሽታውን ለመለየት የሚደረጉ ምርመራዎች ደም ወይንም ሌላ ከሰውነት የመነጨ ፈሳሽ (ሽንት፤አክታ፤ሰገራ፤መግል፤የሳምባሽንት፤ አክታ፤ ሰገራ፤ መግል፤ የሳምባ ልባስ ፈሳሽ፤ ወዘተ) ሊያካትቱ ይችላል፡፡
 
በተለያዩ በሽታዎች ምክንያት የሚመጡ የተለየ ምልክት የሚሰጡ ጉልህ የሆኑ የአካላት ላይ የቅርፅ ለውጦችን በማየትም በሽታው ምን እንደሆነ ለመለየት የሚቻል ሲሆን፤ እነኚህን ለውጦች ለማየት በመሳሪያ የታገዘ ቀጥተኛ የሆነ የውስጥ አካል እይታ (ኤንዶስኮፒ)፤ በድምፅ-መሰል ሞገዶች የታገዘ የአልትራሳውንድ ምርመራ፤ ወይንም ኤክስ ሬይ (ራጅ) እና ሌሎች ጠልቆ ለማየት የሚያስችሉ ምርመራዎች ይታዘዛሉ፡፡