ከ«ኣበራ ሞላ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
No edit summary
No edit summary
መስመር፡ 16፦
 
===የግዕዝ ቀለሞች===
ከልጃቸው ብሩክ ጋር የመጀመሪያውን የግዕዝ የእስክሪንና የማተሚያ ቀለሞች ለመሥራት ኣንድ ዓመት ግድም ነበር የወሰደው። [http://archive.is/uKbLy] የፊደሉም ችሎታ በማደግ መጀመሪያ ፖስትእስክሪፕት ከእዚያም በ፲፱፻፹፩ ዓ.ም. ትሩታይፕ [http://sirius-c.ncat.edu/EAS/news/EJSciTech/abera2.html] በኋላም ተንቀሳቃሽ (Embedable) ሆኗል። ግዕዝ ወደ ኮምፕዩተር ሲገባ የስምንት እንግሊዝኛ ሥፍራዎችን በማስለቀቅ ዓይነት ኣንዱኑ ቦታ በየተራ በመጋራት ነበር። በዩኒኮድ መፈጠር የተነሳ ዶ/ር ኣበራ ኮምፕዩተራይዝ የኣደረጉት እየኣንድኣንዱ ቀለም የእራሱን ስፍራ ኣግኝቷል። Aberra Molla ከዓለም ፊደል ሠሪዎች ኣንዱ ናቸው። [https://graviranje.rs/Engraving_PORTAL/fonts/Font_Designers.htm] ብዙዎቹ የግዕዝ ቀለሞች በዓለም የፊደላት መደብ ዕውቅና ከኣገኙበት ከ፲፱፻፹፫ ዓ.ም. ግድም ወዲህ ግን የዕውቀት ክምችት እንዲስፋፋ በቀለሞቹ እንደመጠቀም ዛሬም ኋላቀር በሆነው የኣማርኛ የታይፕ መጻፊያው ዓይነት ቅጥልጥል የኣማርኛ ፊደላት እየጻፉ ኢትዮጵያንና እራሳቸውን ወደኋላ እየጎተቱ ያሉትን እየተቃወሙ ነው። [http://sirius-c.ncat.edu/asn/country/ethiopia/AAU-Network/news/EJSciTech/abera2.html] ትክክለኛዎቹና ሁሉም የግዕዝ ቀለሞች የዩኒኮድ መደብ ውስጥ እንዲገቡ ዶክተሩ ትልቅ ትግልና ኣስተዋጽዖም ኣድርገዋል። ለምሳሌ ያህል በመጀመሪያ ዙር ዶክተሩ ኮምፕዩተራይዝ የኣድረጉትየኣደረጉት እንጂ የታይፕራይትሩ ፊደል ግዕዝ እንዳልሆነ ተገልጿል። [http://web.archive.org/web/20060516083455/http://www.ethiopic.com/unicode/Ethiopic%20Computerization.htm] ይኸን [http://web.archive.org/web/20121227134618/http:/www.ethiopic.com/unicode.htm] ግዕዝ የኣልሆነ ቊርጥራጭ የኣማርኛ ታይፕራተር ዓይነት ፊደል የግዕዝ ፊደል ስለኣልሆነ በሁለተኛ ዙር ተቃውመው ኣስጥለዋል። [http://web.archive.org/web/20121031103452/http://www.ethiopic.com:80/advances.htm] የዶክተሩ ሦስተኛ ዙር ተቃውሞ የዓማርኛውን የማተሚያ ቤት ፊደላት ለዩኒኮድ እ.ኤ.ኣ. በ1992 የቀነጠሱትን [http://web.archive.org/web/20121227134618/http:/www.ethiopic.com/unicode.htm] እና የኣናሳ ተጠቃሚዎች ፊደላት በቍርጥራጭ ፊደላት እንዲተኩ እ..ኤ.ኣ. በ1993 የፈለጉትንና የኣማርኛ ፊደላት ቅነሳ ውስጥ የገቡትንም ያጠቃላል። [http://www.ethiopians.com/abass7.html] ዶክተሩ ዲጂታይዝ የኣደረጉት የግዕዝ ፊደል የኢትዮጵያ ማተሚያ ቤቶች ሲጠቀሙባቸው በነበሩት ፊደላት ሲታተሙ ስለነበሩና ስለሆኑ ዛሬ ወደ ፒ.ዲ.ኤፍ (P.D.F.) የተቀየሩትን ጭምር ያለ ችግር ማንበብ ተችሏል።
 
ፊደሉንም ለማሟላትና ከሌሎች ፊደላት እኩል እንዲራመዱ በየጊዜው ጽፈዋል። ለምሳሌ ያህል እነ “ሀ”፣ “ሐ”፣ “ኀ”፣ “አ”፣ እና “ዐ” የተሳሳቱ ድምፆች ተሰጣቸው እንጂ በዶ/ር ኣበራ ገለጻ የእየራዕቦቻቸው ሞክሼዎች ስለኣልሆኑ ለማጥፋት ማዘጋጀት ቀርቶ ድምፆቻቸውን ተረክበው መብታቸው መከበር ኣለበት ነው። ዕውቀቱም ከዩኒቨርሲቲ ወደ ሕዝቡ መድረስ ኣለበት። [http://www.fhlethiopia.com/uploads/2/8/0/2/2802756/____.pdf] ይህ ትግርኛውንም ይመለከታል። ዓማርኛ፣ [[ቤንች]]ና [[ጉሙዝ]] የቋንቋ ዋና ክፍሎች የ“ጨ” ቀለሞች፣ እንዚራንና ዘመዶች ቀለበቶች ሦስት ሳይሆኑ ሁለት ናቸው። የ“ሀ” ትክክለኛ ድምጽ ወደ “ኸ” የቀረበ ቢሆንም “ኸ”ም የዓማርኛ ሞክሼ የሚባለው ዓይነት ቀለም ስለኣልሆነ ነው ግዕዝ ኮምፕዩተራይዝ ሲደረግ የምልክት መርገጫዎች ላይ የመርገጫ ስም የተሰጠው። የ“አ” ድምጽ በስሕተት “ኧረ” የሚለው ቃል ምሳሌ ውስጥ ስንጠቀምበት የነበረ ድምጽ ስለሆነ ለ“ኧ” ስምንተኛው የ“አ” ቤት ፊደል ድምፁን ዶክተሩ መልሰው ኣስረክበውታል። [“ኧረ”] መከተብ ያለበት በ“አረ” ነው። ምክንያቱም የስምንተኛው ድምጽ ቀለም የሚሠ'ራው ግዕዙ ወይም ራብዑ ላይ መስመር በመጨመር ስለሆነና የ“አ” ቤት ስምንተኛ ቀለም የማይኖርበት ምክንያት ስለሌለ ነው። ይህ የዓይኑ “ዐ” ባለመስመር “ዓ”ንም ሊመለከት ይችላል። “ኧ” የስምንተኛው የ“አ” ቤት ቀለም ስለሆነ ስምንተኛውን የ“አ” ቤት ድምጽ (ወደ “እዋ” የቀረበውን) ለ“ኧ” ፊደል መስጠቱ ተገቢ ይመስላል። [http://www.ethiopic.com/amharic/errors.pdf] የ“የ”ም ስምንተኛ ድምጽ ቀለም ኣለ። የ“ሀ”ም አንዲሁ። ግዕዝ ድምፃዊ ፊደል (Syllabic) ስለሆነ “ሀ” እና “ሃ” ወይም “አ” እና “ኣ” ድምጽ ስለማይጋሩ ነው ዶክተሩ ስማቸውን “ኣበራ” እንጂ “አበራ” በማለት የማይጽፉት። [http://dagmawibelete.blogspot.com/2013/05/ethiopic.html] [http://web.archive.org/web/20130109102454/http://www.ethiopic.com/ethiopic_alphabet.htm] ከምክንያቶቹ ኣንዱ የግዕዝ ቤቶቹ ቅርሶች ሲጠሩ እንደራብዖቹ ኣፍ በሰፊው ስለማያስከፍቱ ነው።