Content deleted Content added
Praxidicae (ውይይት | አስተዋጽኦ) ጥ delete |
Praxidicae (ውይይት | አስተዋጽኦ) Rvv |

መስመር፡ 1፦
{{መለጠፊያ:ዋቢ
|ቀን=፬ ነሐሴ ፳፻፮

{{የሀገር መረጃ
|ስም = ኢትዮጵያ
|ሙሉ_ስም = የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ
|ማኅተም_ሥዕል = Coat of arms of Ethiopia.svg
|ባንዲራ_ሥዕል = Flag of Ethiopia.svg
|ባንዲራ_ስፋት =
|መዝሙር = [[ወደፊት ገስግሺ፣ውድ እናት ኢትዮጵያ]]

[[ስዕል:Wedefit Gesgeshi Widd Innat Ittyoppya.ogg]]
|ካርታ_ሥዕል = Ethiopia in its region.svg
|ካርታ_መግለጫ_ፅሁፍ = ኢትዮጵያ |ካርታ_መግለጫ_ፅሁፍ = ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ቀለም
|ዋና_ከተማ = [[አዲስ አበባ]]
|ብሔራዊ_ቋንቋ = [[አማርኛ]] ሌሎች ቋንቋዎች ክልላዊ ዕውቅና አላቸው
|የመንግስት_አይነት = ፌዴራላዊ ሪፐብሊክ
|የመሪዎች_ማዕረግ = [[ፕሬዝዳንት]]
[[ጠቅላይ ሚኒስትር]]
|የመሪዎች_ስም = ወ/ሮ [[ሳህለወርቅ ዘውዴ]]
ዶ/ር [[አብይ አህመድ]]
|ታሪካዊ_ቀናት =
|ታሪካዊ_ክስተቶች =
|የመሬት_ስፋት = 1,104,300
|የመሬት_ስፋት_ከዓለም = 26
|ውሀ_ከመቶ =
0.7
|የሕዝብ_ብዛት_ግምት_ዓመት = ፳፻ |የሕዝብ_ብዛት_ግምት_ዓመት = ፳፻ ዓ.ም.
|የሕዝብ_ብዛት_ቆጠራ_ዓመት = |የሕዝብ_ብዛት_ቆጠራ_ዓመት = ፲፱፻፺፱ ዓ.ም.
|የሕዝብ_ብዛት_ግምት = |የሕዝብ_ብዛት_ግምት = 93,578,567
|የሕዝብ_ብዛት_ቆጠራ = |የሕዝብ_ብዛት_ቆጠራ =
96,787,564
|የሕዝብ_ብዛት_ከዓለም = 13
|የገንዘብ_ስም = ብር
|ሰዓት_ክልል = +3
|የስልክ_መግቢያ = 251
|ከፍተኛ_ደረጃ_ከባ|ከፍተኛ_ደረጃ_ከባቢ = .et
|የግርጌ_ማስታወሻ =

'''ኢትዮጵያ''' ወይም በይፋ '''የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ (ኢ.ፌ.ዲ.ሪ.)''' በ[[የአፍሪካ ቀንድ|አፍሪካ ቀንድ]] የምትገኝ የረጅም ዘመን [[ታሪክ]] ያላት ሀገር ናት። በ[[አፍሪካ]] ነፃነታቸውን ጠብቀው ለመኖር ከቻሉ ሁለት [[አገሮች]] አንዷ ነች። በህዝብ ብዛት ከአፍሪካ ኢትዮጵያ ሁለተኛ ስትሆን ፣ በቆዳ ስፋት ደግሞ አስረኛ ናት። [[ዋና ከተማ|ዋና ከተማ]]ዋ [[አዲስ አበባ]] ናት።
አብዛኛዎቹ የአፍሪካ ሀገሮች ዕድሜያቸው ከአንድ ምዕተ-ዓመት የሚያንስ ሲሆን ፣ ኢትዮጵያ ግን ከጥንት ጊዜ ጀምሮ [[ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ|በንጉሠ-ነገሥታት]] እና ንግሥተ-ነግሥታት የተመራች ሀገር ናት። የ[[ሰለሞናዊው ሥርወ-መንግሥት]] የአመጣጡን ዘር እስከ አስረኛው ዓመተ-ዓለም ድረስ ይቆጥራል። ኢትዮጵያ [[የሰው ልጅ]] ከጥንት ጊዜ ጀምሮ የኖረባት ቦታ እንደሆነች ብዙ የሳይንሳዊ መረጃ ተግኝቷል። በ[[የበርሊን ጉባኤ|በርሊን ጉባኤ]] በኩል የአውሮፓ ሀያላት ሀገሮች አፍሪካን ሲከፋፍሏት፣ ኢትዮጵያ ነፃነቷን ጠብቃለች። የ[[ሊግ ኦፍ ኔሽንስ|ሊግ ኦፍ ኔሽንስ (''League of Nations'')]] አባል ከነበሩት ሶስት የአፍሪካ ሀገሮች አንዷ ነበረች። ከአጭር [[የኢጣልያ ወረራ]] ጊዜ በኋላም ከ[[የተባበሩት መንግሥታት]] መሥራቾች አንዷ ናት። ከ[[ሁለተኛው የዓለም ጦርነት]] በኋላ ብዙ የአፍሪካ ሀገራት ነፃነታቸውን ሲያገኙ፣ [[ሰንደቅ አላማ|ሰንደቅ-አላማቸውን]] በኢትዮጵያ ቀለሞች ማለትም በ[[አረንጓዴ]] ፣ [[ቢጫ]] እና [[ቀይ]] ላይ ነው የመሠረቱት። አዲስ አበባ ደግሞ ለየተለያዩ በአፍሪካ ላይ ላተኮሩ አለም አቀፍ ድርጅቶች መቀመጫ ሆነች።
የዛሬዋ ኢትዮጵያ የትልቅ የግዛት ለውጥ ውጤት ናት። ከሰሜን ግዛቱዋ በጣም የተቀነሰ ሲሆን በደቡብ በኩል ደግሞ ተስፋፍቷል። በ [[1967|፲፱፻፷፯ (1967)]] ዓ.ም.፣ [[ግርማዊ ቀዳማዊ ዓፄ ኃይለ ሥላሴ]] ከሥልጣን ሲወርዱ፣ የእርስ በርስ ጦርነት በሀገሩ ተባባሰ። ከዚህ ጊዜ በኋላ ኢትዮጵያ በተለያዩ የመንግሥት አይነቶች ተዳድራለች። ዛሬ አዲስ አበባ [[የአፍሪካ ሕብረት]] (''African Union'') እና [[የተባበሩት መንግሥታት የኢኮኖሚክ ኮሚሽን ለአፍሪካ]] መቀመጫ ናት። የኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት ከአፍሪካ ኃያል ሠራዊቶች አንዱ ነው። ኢትዮጵያ በአፍሪቃ የእራሷ ጥንታዊ ፊደል ያላት ሀገርም ናት።
ኢትዮጵያ ተፈጥሮ ያደላት ሀገር ናት። ከአፍሪካ ትላልቅ ተራራዎች እንዲሁም ከዓለም ከባህር ጠለል በታች በጣም ጥልቅ ከሆኑ ቦታዎች አንዳንዶቹ ይገኙባታል። [[ሶፍ ዑመር]] ከአፍሪካ ዋሻዎች ትልቁ ሲሆን ፣ [[ዳሎል]] ከዓለም በጣም ሙቅ ቦታዎች አንዱ ነው። ወደ ሰማንኒያ የሚቆጠሩ ብሔሮችና ብሔረሰቦች ዛሬ በኢትዮጵያ ይገኛሉ። ከእነዚህም [[ኦሮሞ]]ና [[አማራ]] በብዛት ትልቆቹ ናቸው። ኢትዮጵያ በኣክሱም ሓውልት፣ ከአንድ ድንጋይ ተፈልፍለው በተሰሩ ቤተ-ክርስትያኖቹዋ እና በ[[ኦሎምፒክ]] የ[[ወርቅ]] ሜዳልያ አሸናፊ አትሌቶቹዋ ትታወቃለች። የ[[ቡና]] ፍሬ ለመጀመሪያ ጊዜ የተገኘው በኢትዮጵያ ሲሆን ሀገሪቱዋ በቡናና [[ማር]] አምራችነት በአፍሪካ ቅድሚያ ይዛለች።
ኢትዮጵያ ከዓለም ሶስቱ ትላልቅ የአብርሃም ሀይማኖቶች ጋር ታሪካዊ ግንኙነት አላት። [[ክርስትና]]ን በአራተኛው ምዕተ-ዓመት ተቀብላለች። ከሕዝቡ አንድ ሁለተኛው [[ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ክርስትና]] ነው። የመጀመሪያው የእስላም [[ሂጅራ]] ወደ ኢትዮጵያ ነው የተከናወነው። [[ነጋሽ]] በአፍሪካ የመጀመሪያው የእስላም መቀመጫ ናት። እስከ ፲፱፻፸ ዎቹ ድረስ ብዙ [[ቤተ እስራኤል|ቤተ-እስራኤሎች]] በኢትዮጵያ ይኖሩ ነበር። የ[[ራስ ተፈሪ እንቅስቃሴ]] ኢትዮጵያን በትልቅ ክብር ነው የሚያያት።
ግርማዊ ቀዳማዊ ዓፄ ኃይለ ሥላሴ ከስልጣን ከወረዱ በኋላ ድህነት በኢትዮጵያ በጣም ተስፋፍቶ ነበር። ሰማኒያ አምስት ከመቶ በላይ የሚሆነው የ[[ናይል]](ኣባይ) ወንዝ ውሀ ከሀገሩ የሚመጣ ቢሆንም በ ፲፱፻፸ ዎቹ በተከሰቱ ድርቆች በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች ሞተዋል። ነገር ግን ቀስ በቀስ ሀገሩዋ እያገገመች ነው። ዛሬ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በአፍሪካ ውስጥ በፍጥነት ከሚያድጉት አንዱ ነው።
=D=
=B=