ከ«ዒዛና» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
No edit summary
Tags: በንፋስ ስልክ -የሞባይል ድረገፅ
No edit summary
Tags: በንፋስ ስልክ -የሞባይል ድረገፅ
መስመር፡ 19፦
'''ዒዛና''' (በ[[ግሪክ (ቋንቋ)|ግሪክ]] ፡ '''ኤይዛናስ''') ፣ (ወደ ፬ኛው ክ/ዘ አጋማሽ ዓ.ም.) ፣ ከ[[አክሱም]] ነገስታት ሁሉ ገናና የሆነ የመጀመሪያው ክርስትያን ንጉሥ ነበር ። ምናልባት ለአባቱ ለንጉሥ [[ኢላ-አሚዳ]] ፡ የበኩር ልጁ ሳይሆን አይቀርም ። ስለ እናቱ ሥም የሚናገር [[ታዓማኒ]] የጽሑፍ መረጃ እስካሁን ድረስ አልተገኘም ። ከሁለተኛ ደረጃ ምንጮች መሠረት ግን የእናቱ ሥም [[ሶፍያ]] ይባላል ።
 
ሁለቱ ወንድሞቹ [[ሣይዛና]] እና [[ኃደፋ]] በአስተዳደር እና በውትድርና ሥራዎች ይረዱት ነበር ። በተለያዩ ጊዜያት ባደረጋቸው ተከታታይ የግዛት ማስፋፍያ ዘመቻዎች ፡ ንጉሥ ዒዛና ግዛቱን በስሜን [[ቤጃ]]ዎች፣ [[ካሡ]]ና [[ኖባ]] በተባሉ የተከዘ ቀበሌዎች ፣ በ[[አትባራ]] እና በ[[አባይ ወንዝ (ናይል)|አባይ]] ወንዞች ፣ በምስራቅ በኩል በ[[አግወዛት]] ፣ በደቡብ [[ስራኔ]] በተባለ የአፋን ምድሮች ላይ ወረራ እንደፈጸመ በ[[ግዕዝ]] ፣ በጥንታዊ [[ዐረብኛ]] ፣ እና በ[[ግሪክ (ቋንቋ)|ግሪክ]] ተጽፈው በ[[አክሱም]] የተገኙ የጽሑፍ መረጃዎች ያመለክታሉ ። የግዛት ማስፋፍያ ዘመቻዎቹ ቅደም ተከተል ግን እስካሁን አከራካሪ ናቸው ።
== የዒዛና የጦር ስልት ==
ንጉሥ ዒዛና ከሚጠቀሱለት የአስተዳደር ባሕርያት ውስጥ፤ የተቀናቃኞችን እና የአመፀኞችን ግዛቶች ካስገበረ በኋላ በምሕረትና በበጎ አስተዳደር ሥርዓት መተካቱ ፣ የአመፀኞችን ኃይል ለመስበር የሚያደርጋቸው የርስት ነቀላና የተለዋጭ ሠፈራ እርምጃዎች ተጠቃሽ ናቸው ። የዙፋኑ ሥያሜም ፦ ዒዛና የአክሱም፣ [[ሒምያር]] ፣ [[ራይዳን]] ፣ [[ሣባ (የአረቢያ ግዛት)|ሳባ]] ፣ [[ሳልሄን]] ፣ [[ሲያሞ]] ፣ [[ቤጋ]] ([[ቤጃ]]) እና [[ካሡ]] ንጉሥ ነበር ።
== የግዛቱ ክልል ==
የደቡብ ዓረብያ ግዛቶች ሥም በዙፋኑ ሥያሜ መካተታቸው ከንጉሣዊ ራዕይ ወይም ምኞት የመነጩ እንጂ በእርግጥም በግዛቱ የተጠቃለሉ የባሕር ማዶ አውራጃዎች ናቸው ለማለት የሚያበቃ በቂ መረጃ የለም ። ከወርቅ፣ ከብር እና ከነሓስ በተቀረጹት ገንዘቦቹ ላይ «ዒዛና ዘሐለን ፣ የአክሱሞች ንጉስ» የሚል ጽሑፍ ይነበባል።
== ንግድን በሚመለከት ==
 
በንጉሥ ዒዛና ዘመን ፡ አክሱማውያን በዓለም-ዓቀፍ ንግድ ረገድ እንደ ዝሆን ጥርስ፣ ወርቅ፣ የዔሊ ክዳን ፣ ቆዳ፣ ቅመማ ቅመም ወዘተ ወደ ውጭ ይልኩ እንደነበር፤ እንዲሁም ከወደ [[ሕንድ]] የሚመጡ ሽቀጦችን በመጨመር ከ[[ግሪኮች]]ና ከ[[ሮማዊያን]] ጋር የ[[አዱሊስ]] ወደብን በመጠቀም የንግድ ልውውጥ ያካሂዱ እንደነበር፣ በመዲናዋም የውጪ ዜጎችን ጨምሮ፣ ነጋዴዎች እና በልዩ ልዩ የሙያ መስኮች የተስማሩ በርካታ ነዋሪዎች ይኖሩባት እንደነበር መረጃዎች ያመለክታሉ ።
== ሃይማኖትን በሚመለከት ==
 
በንጉሥ ዒዛና ዘመን ዋንኛው ተጠቃሽ ክስተት [[ክርስትና]]ን ከ[[ፍሬምናጦስ]] አምኖ መቀበሉ ነው ። ሆኖም የክርስትና እምነት ወደ [[ኢትዮጵያ]] በ 4ኛው ክ/ዘ የመጀመሪያ ዓስርተ ዓመታት ውስጥ ቀደም ብሎ መግባት ጀምሮ ነበር ። በቅድመ ክርስትና ዘመኑ ፡ ንጉሥ ዒዛና [[አስቴር]] ፣ [[መድር]] ፣ [[ቤኄር]] ፣ [[ሜኅረም]] ፣ [[አረስ]] በተባሉ አማልክት ያምን እንደነበረና እራሱንም የነዚህ አማልክት ልጅ አድርጎ ይቆጥር እንደነበር በጽሑፍ የተገኙ መረጃዎች ያሳያሉ ። በኋለኛ ዘመኖቹ ደግሞ የአሃዳዊ መለኮታዊ አምላክ አማኝ ስለመሆኑ የሚመስክሩ ጽሑፎች ተገኝተዋል ። በ 1969 በተገኘ የመረጃ ሰነድ ላይ ፡ ንጉሥ ዒዛና በግልፅ ክርስትያን ስለመሆኑ ሳያሻማ ይናገራል ። በዘመኑ የተቀረፁት ሳንቲሞቹ ላይ የጨረቃና-ኮከብ የቅድመ ክርስትና ምልክቶች ቀስ በቀስ ፡ የመስቀል ምልክቶች ባላቸው ሳንቲሞች እየተተኩ ሄደዋል ። እንዲሁም የአርያኖች ንጉሥ [[ቆንስጣንጢኖስ]] (፫፻፳፱-፫፻፶፫) የላከው «ለተወደዱት ሁለት ወንድሞቼ ዒዛና እና ሳይዛና ፡ የአክሱም ነገስታት» በማለት የሚጀምረው ታሪካዊ ደብዳቤ ስለ ፍሬምናጦስ ጵጵስና እና ዕውቅና ጉዳይ በሚመለከት ግለስቡን ወደ [[እስክንድርያ ፓትርያርክ]] [[አትናቴዎስ]] ዘንድ እንዲልኩት የሚጠይቀው ይህ ደብዳቤ እንደ ተጨማሪ መረጃ የሚያገለግል ስነድ ነው ። ፍሬምናጦስን ከዚሁ ደብዳቤ መላክ ሃያ አምስት ዓመት ቀደም ብሎ በኢትዮጵያ ጳጳስ አድርጎ ሾሞ የላከው ይኸው ንጉስ አትናቴዎስ ነበር ።
== መታወቂያው ==
 
በነገስታት ዝርዝር ላይ የንጉሥ ዒዛና ሥም አለመታወቁ ያስገርማል ። ሆኖም በሳንቲሞቹ ላይ ያለው ሥምይኸው «ዒዛና» የሚለው ነው ያለው ። በዘልማድ እንደሚነገረው ግን ፡ ንጉሥ [[አብርሃ]] እና ወንድሙ [[አጽብሃ]] ክርስትና ወደ ኢትዮጵያ በገባበት ዘመን ኢትዮጵያን የሚገዙ ወንድማማች ንጉሦች ነበሩ ። ምናልባት ክርስትናን በተቀበሉበት ጊዜ የወስዱት የክርስትና ሥማቸው ሊሆን ይችላል ።