ከ«የጁ ስርወ መንግስት» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
No edit summary
አንድ ለውጥ 352898 ከ197.156.85.249 (ውይይት) ገለበጠ
Tag: Undo
መስመር፡ 1፦
'''የየጁ ስርወ መንግስት''' በወሎ አንደኛው ክፍል ነው:: ከ18ኛው ክፍለዘመን መጨረሻ እስከ 19ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ ድረስ ተጠናክረው ኢትዮጵያን በእንደራሴነት ሲያገለግሉ የነበሩ ራሶችን የሚገልጽ ነው። በዚህ ዘመን የ[[ጎንደር]] ነገስታት ሃይል እጅግ ከማሽቆልቆሉ የተነሳ እኒ እንደራሴወች የፈለጉትን ከስልጣን የማንሳትና የፈለጉትን የመሾም ሃይሉ ነበራቸው። ስለዚህም የአገሪቱ መሪ ነበሩ ቢባል ማጋነን አይሆንም። ከየጁ ስርወ መንግስት እንደራሴወች፡ [[ራስ ዓሊ ትልቁ]] [[ ራስ ዓሊጋዝ]] [[ራስ ጉግሣ]] [[ራስ ይማም]] [[ራስ ማርዬ]] [[ራስ ዶሪ]] [[ራስ ዓሊ ትንሹ]]
 
የየጁ መሪወች አብዛኛውን ጊዜ የ[[የጁ ኦሮሞ]] ተብለው ቢታወቁም አነሳስቸው በበለጠ እጅግ የተወሳሰበ ነው። የጁወች በድሮ ዘመን [[ደቡብ ሴማዊ]] ቋንቋ የሚናገሩ ህዝቦች ነበሩ። የሚኖሩበትም አገር [[ቀወት]] ይባል ነበር፤ ይህም በ[[ይፋት]]፣ [[ሸዋ]] ነበር። የ[[ግራኝ አህመድ]] ሰራዊት እኒህን ህዝቦች በቀወት ለመጀመሪያ ጊዜ እንዳገኛቸው [[ሺሃብ አድ-ዲን]] የተሰኘው ዜና መዋዕል ጸሃፊው ዘግቧል። ከዚህ በኋል በ16ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ የጁወች ብዙ ኦሮሞወችን ተቀብለዋል። ስለዚህም በቀጣዩ ዘመናት የየጁ ኦሮሞወች ተባሉ።