ከ«የማቴዎስ ወንጌል» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
Tags: በንፋስ ስልክ -የሞባይል ድረገፅ
Tags: በንፋስ ስልክ -የሞባይል ድረገፅ
መስመር፡ 869፦
**፤ስታቴር፡ኹለት፡ብር፡ያኽል፡ነው።
== '''ምዕራፍ ፲፰''' ==
1፤በዚያች፡ሰዓት፡ደቀ፡መዛሙርቱ፡ወደ፡ኢየሱስ፡ቀርበው፦በመንግሥተ፡ሰማያት፡ከዅሉ፡የሚበልጥ፡ማን፡
ይኾን፧አሉት።
2፤ሕፃንም፡ጠርቶ፡በመካከላቸው፡አቆመ፡
3፤እንዲህም፡አለ፦እውነት፡እላችዃለኹ፥ካልተመለሳችኹ፡እንደ፡ሕፃናትም፡ካልኾናችኹ፥ወደ፡መንግሥተ፡
ሰማያት፡ከቶ፡አትገቡም።
4፤እንግዲህ፡እንደዚህ፡ሕፃን፡ራሱን፡የሚያዋርድ፡ዅሉ፥በመንግሥተ፡ሰማያት፡የሚበልጥ፡ርሱ፡ነው።
5፤እንደዚህም፡ያለውን፡አንድ፡ሕፃን፡በስሜ፡የሚቀበል፡ዅሉ፡እኔን፡ይቀበላል፤
6፤በእኔም፡ከሚያምኑ፡ከነዚህ፡ከታናናሾቹ፡አንዱን፡የሚያሰናክል፡ዅሉ፥የወፍጮ፡ድንጋይ፡በዐንገቱ፡ታስሮ፡
ወደ፡ጥልቅ፡ባሕር፡መስጠም፡ይሻለው፡ነበር።
7፤ወዮ፡ለዓለም፡ስለ፡ማሰናከያ፤ማሰናከያ፡ሳይመጣ፡አይቀርምና፥ነገር፡ግን፥በርሱ፡ጠንቅ፡ማሰናከያ፡
ለሚመጣበት፡ለዚያ፡ሰው፡ወዮለት።
8፤እጅኽ፡ወይም፡እግርኽ፡ብታሰናክልኽ፥ቈርጠኽ፡ከአንተ፡ጣላት፤ኹለት፡እጅ፡ወይም፡ኹለት፡እግር፡
ኖሮኽ፡ወደዘለዓለም፡እሳት፡ከምትጣል፡ይልቅ፡ዐንካሳ፡ወይም፡ጕንድሽ፡ኾነኽ፡ወደ፡ሕይወት፡መግባት፡
ይሻልኻል።
9፤ዐይንኽ፡ብታሰናክልኽ፡አውጥተኽ፡ከአንተ፡ጣላት፤ኹለት፡ዐይን፡ኖሮኽ፡ወደ፡ገሃነመ፡እሳት፡ከምትጣል፡
ይልቅ፡አንዲት፡ዐይን፡ኖራኽ፡ወደ፡ሕይወት፡መግባት፡ይሻልኻል።
10፤ከነዚህ፡ከታናናሾቹ፡አንዱን፡እንዳትንቁ፡ተጠንቀቁ፤መላእክታቸው፡በሰማያት፡ዘወትር፡በሰማያት፡ያለውን፡
የአባቴን፡ፊት፡ያያሉ፡እላችዃለኹና።
11፤የሰው፡ልጅ፡የጠፋውን፡ለማዳን፡መጥቷልና።
12፤ምን፡ይመስላችዃል፧ላንድ፡ሰው፡መቶ፡በጎች፡ቢኖሩት፡ከነርሱም፡አንዱ፡ቢባዝን፥ዘጠና፡ዘጠኙን፡
በተራራ፡ትቶ፡ኼዶም፡የባዘነውን፡አይፈልግምን፧
13፤ቢያገኘውም፥እውነት፡እላችዃለኹ፥ካልባዘኑቱ፡ከዘጠና፡ዘጠኙ፡ይልቅ፡በርሱ፡ደስ፡ይለዋል።
14፤እንደዚሁ፡ከነዚህ፡ከታናናሾቹ፡አንዱ፡እንዲጠፋ፡በሰማያት፡ያለው፡አባታችኹ፡ፈቃድ፡አይደለም።
15፤ወንድምኽም፡ቢበድልኽ፥ኼደኽ፡አንተና፡ርሱ፡ብቻችኹን፡ኾናችኹ፡ውቀሰው።ቢሰማኽ፥ወንድምኽን፡
ገንዘብ፡አደረግኸው፤
16፤ባይሰማኽ፡ግን፥በኹለት፡ወይም፡በሦስት፡ምስክር፡አፍ፡ነገር፡ዅሉ፡እንዲጸና፥ዳግመኛ፡አንድ፡ወይም፡
ኹለት፡ከአንተ፡ጋራ፡ውሰድ፤
17፤እነርሱንም፡ባይሰማ፥ለቤተ፡ክርስቲያን፡ንገራት፤ደግሞም፡ቤተ፡ክርስቲያንን፡ባይሰማት፥እንደ፡አረመኔና፡
እንደ፡ቀራጭ፡ይኹንልኽ።
18፤እውነት፡እላችዃለኹ፥በምድር፡የምታስሩት፡ዅሉ፡በሰማይ፡የታሰረ፡ይኾናል፥በምድርም፡የምትፈቱት፡
ዅሉ፡በሰማይ፡የተፈታ፡ይኾናል።
19፤ደግሞ፡እላችዃለኹ፥ከእናንተ፡ኹለቱ፡በምድር፡በማናቸውም፡በሚለምኑት፡ነገር፡ዅሉ፡ቢስማሙ፡በሰማያት፡ካለው፡ከአባቴ፡ዘንድ፡ይደረግላቸዋል።
20፤ኹለት፡ወይም፡ሦስት፡በስሜ፡በሚሰበሰቡበት፡በዚያ፡በመካከላቸው፡እኾናለኹና።
21፤በዚያን፡ጊዜ፡ጴጥሮስ፡ወደ፡ርሱ፡ቀርቦ፦ጌታ፡ሆይ፥ወንድሜ፡ቢበድለኝ፡ስንት፡ጊዜ፡ልተውለት፧እስከ፡ሰባት፡ጊዜን፧አለው።
22፤ኢየሱስ፡እንዲህ፡አለው፦እስከ፡ሰባ፡ጊዜ፡ሰባት፡እንጂ፡እስከ፡ሰባት፡ጊዜ፡አልልኽም።
23፤ስለዚህ፥መንግሥተ፡ሰማያት፡ባሮቹን፡ሊቈጣጠር፡የወደደን፡ንጉሥ፡ትመስላለች።
24፤መቈጣጠርም፡በዠመረ፡ጊዜ፥እልፍ፡መክሊት፡ዕዳ፡ያለበትን፡አንድ፡ሰው፡ወደ፡ርሱ፡አመጡ።
25፤የሚከፍለውም፡ቢያጣ፥ርሱና፡ሚስቱ፡ልጆቹም፡ያለውም፡ዅሉ፡እንዲሸጥና፡ዕዳው፡እንዲከፈል፡ጌታው፡አዘዘ።
26፤ስለዚህ፥ባሪያው፡ወድቆ፡ሰገደለትና፦ጌታ፡ሆይ፥ታገሠኝ፥ዅሉንም፡እከፍልኻለኹ፡አለው።
27፤የዚያም፡ባሪያ፡ጌታ፡ዐዘነለትና፡ለቀቀው፥ዕዳውንም፡ተወለት።
28፤ነገር፡ግን፥ያ፡ባሪያ፡ወጥቶ፡ከባልንጀራዎቹ፡ከባሮቹ፡መቶ፡ዲናር፡ዕዳ፡ያለበትን፡አንዱን፡
አገኘና፦ዕዳኽን፡ክፈለኝ፡ብሎ፡ያዘና፡ዐነቀው።
29፤ስለዚህ፥ባልንጀራው፡ባሪያ፡ወድቆ፦ታገሠኝ፥ዅሉንም፡እከፍልኻለኹ፡ብሎ፡ለመነው።
30፤ርሱም፡አልወደደም፥ግን፡ኼዶ፡ዕዳውን፡እስኪከፍል፡ድረስ፡በወህኒ፡አኖረው።
31፤ባልንጀራዎቹ፡የኾኑ፡ባሪያዎችም፡ያደረገውን፡አይተው፡እጅግ፡ዐዘኑ፥መጥተውም፡የኾነውን፡ዅሉ፡
ለጌታቸው፡ገለጡ።
32፤ከዚያ፡ወዲያ፡ጌታው፡ጠርቶ፦አንተ፡ክፉ፡ባሪያ፥ስለ፡ለመንኸኝ፡ያን፡ዕዳ፡ዅሉ፡ተውኹልኽ፤
33፤እኔ፡እንደ፡ማርኹኽ፡ባልንጀራኽ፡የኾነውን፡ያን፡ባሪያ፡ልትምረው፡ለአንተስ፡አይገ፟ባ፟ኽምን፧አለው።
34፤ጌታውም፡ተቈጣና፡ዕዳውን፡ዅሉ፡እስኪከፍለው፡ድረስ፡ለሚሣቅዩት፡አሳልፎ፡ሰጠው።
35፤ከእናንተ፡እያንዳንዱ፡ወንድሙን፡ከልቡ፡ይቅር፡ካላለ፥እንዲሁ፡ደግሞ፡የሰማዩ፡አባቴ፡ያደርግባችዃል።
== '''ምዕራፍ ፲፱''' ==