ከ«ጨረቃ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

547 bytes added ፣ ከ1 ዓመት በፊት
no edit summary
የጨረቃ ከአንድ ጫፍ እስከ ሌላኛው ተቃራኒ ጫፍ (diameter) ያለው ርቀት 3,474 ኪሜ (2,159 ማይል) ሲሆን ከመሬት ተመሳሳይ አንድ አራተኛ (1/4 X የመሬት ዲያሜትር) በትንሽ ይበልጣል። የመሬትን አንድ አራተኛ ስፋት ሲኖራት ይዘቷ (volume) ግን የመሬትን ሁለት በመቶ (2%) ብቻ ነው። የጨረቃ ስበት [[የመሬት ስበት]]ን አስራ ሰባት በመቶ (17%) ጋር ይነጻፀራል።
ጨረቃ [[ጨረቃ ላይ መውጣት|የሰው ልጅ ያረፈባት]] ብቸኛዋ የጠፈር አካል ናት።
 
በ[[2011]] [[የቻይና ሕዝባዊ ሪፐብሊክ]] ሳይንቲስቶች ሮቦቶችን ወደ ጨረቃ ልከው የ[[ጎመንዘር]] አይነት (Brassica napus)፣ የ[[ድንች]]ና የ[[ጥጥ]] ዘሮችን በጨረቃ ላይ በመያያዣ ውስጥ ማብቀል እንደተቻለ አስረዱ። ወደፊት ሰዎች ወደ ጨረቃ ቢመልሱ ኖሮ፣ በነዚህ ሦስት ምርቶች፦ ጎመንዘር ለ[[ዘይት]]፣ ድንች ለምግብ፣ ጥጥም ለልብስ፦ እንደሚረዷቸው አሉ።
 
== የቃል ትርጉም እና የስያሜ ታሪክ ==
ይህች የመሬት ብቸኛ ሳተላይት በ[[አማርኛ]] '''ጨረቃ''' ስትሆን በ[[እንግሊዝኛ]]ው ደግሞ ''the Moon'' ትባላላለች። ''Moon'' የ[[ጀርመንኛ]] ቃል ሲሆን ከላቲን ''mensis'' እና ከ[[ጥንታዊ ግሪክ]] ''μήνας'' ተመሳሳይ የሆነ ''ወር'' የሚል ትርጉም አላቸው። ለቃሉ መፈጠር ከወር በተጨማሪ እንደ [[ሰኞ]] እና [[የወር አበባ]] የመሰሉ ቃላት አንድም በ[[እንግሊዝኛ]]ው ትርጉማቸው ከቃሉ ጋር ተመሳሳይ አጀማመር በመኖሩ አልያም በሂደታቸው ርዝማኔ ከ'''ጨረቃ''' ጋር ስለሚገናኙ አስተዋጽዖ አላቸው።
8,739

edits