ከ«ግዑዝነት» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
No edit summary
መስመር፡ 37፦
የዚህ የአዲሱ ሐሳብ መነሻ፣ ''ቁስ አካላት ከፍ ዝቅ በማይል አንድ ፍጥነት እና አንድ ቀጥተኛ አቅጣጫ መጓዝ የተፈጥሮ ፍላጎታቸው'' ነው የሚል ነው። ማለትም በነገሮች ላይ የውጭ ጉልበት እስካለረፈ ድረስ፣ ፍላጎታቸው አርፎ መቆም ብቻ ሳይሆን፣ ሌላም ፍጥነት ካላቸው ከፍ ዝቅ ሳይል በዚያ ፍጥነት መቀጠል ነው። ይህ ግን ከለት ተለት ተሞክሮ የሚቃረን ይመስላል ምክንያቱም በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱ ነገሮች ከውጭ ጉልበት ካላገኙ ምንጊዜም ስለሚቆሙ። ለአሪስጣጣሊስ መሳሳትም ዋናው ምክንያት ይህ ነበር። በምድር ላይ የነገሮች ቆሞ መገኘት ምክንያት በተፈጥሮ ፍላጎታቸው ሳይሆን፣ በ[[ሰበቃ]] [[ጉልበት]] ተገደው ነው። ከምድር፣ ከአየር እና ከሌሎች ቁሶች ጋር በሚያደርጉት ፍትጊያ ምክንያት ቁሶች እንቅስቃሴያቸው ይሞታል። በኦና ውስጥ ቢሆኑ ኖሮ ያለማቋረጥ በተንቀሳቀሱ ነበር።
 
የኤምፒተስን አስተሳብ ግድፈቶች ለማረም የተቻለው በአዲሱ አመለካከት የቁሶችን እንቅስቃሴ በማየት ነበር። አዲሱ አመለካከት፣ ቁሶች ጉልበት ሳያርፍባቸው ሊንቀሳቀሱ መቻላቸው በውስጣቸው እንደክትባት በተወጉት እና በተላለፈላቸው ልዩ ጉልበት አይደለም። ይልቁኑ ቁሶች፣ በተፈጥሮአቸው፣ ያለምንም እርዳታ፣ በአሉበት ፍጥነት፣ [[ቀጥተኛ መስመር|በቀጥተኛ መንገድ]] ለመንቀሳቀስ ይፈልጋሉ። ይህ የቁሶች መሰረታዊ ባህርይ ግዑዝነታቸው (inertia) በመባል ተሰየመ። ስለዚህ ግዑዝነት ማለት፣ በዘመናዊ ትርጓሜው፣ « '''አንድ ቁስ አካል የያዘውን ፍጥነት እንዳይቀየር የሚያሳየው ተቃውሞ'''» ማለት ነው። ሓሳቡ እጅግ የተሳካ ስለነበር፣ እስካሁን ዘመን ድረስ ይሰራበታል።
 
===ድንጋይ ውርወራ ከግዑዝነት ጽንሰ ሐሳብ አንጻር ===