ከ«አካድኛ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
No edit summary
No edit summary
መስመር፡ 1፦
'''አካድኛ''' ወይም '''አሦርኛ''' ወይም '''ባቢሎንኛ''' በጥንት በ[[መስጴጦምያ]] የተናገረ [[ሴማዊ ቋንቋ]] ነበረ።
 
በሥነ ቅርስ መጀመርያው የታወቀው አካድኛ ጽሑፍ ከ[[መስኪአጝ-ኑና]] ዘመን (2314 ዓክልበ. ግድም) ነው። ከ[[አካድ]] ንጉሥ [[ታላቅታላቁ ሳርጎን]] ጀምሮ የአካድ መንግሥት (2077-2010 ዓክልበ.) በመላው መስጴጦምያ፣ [[ኤላም]]ና [[ሶርያ]] አስገደዱት። ከዚያ በኋላ ኤላም ወደ [[ኤላምኛ]] መለሰ፣ የሶርያም ቋንቋ [[ኤብላኛ]] ሆነ። በ[[አሦር]]ና በ[[ባቢሎን]] የአካድኛ አይነቶች ተነገሩ። አሦራውያን በ[[አናቶሊያ]] ([[ሐቲ]]) የ[[ካሩም]] ንግድ እስከ 1628 ዓክልበ. ድርስ ያሕል ያካሄዱ ነበር፤ የአሦርኛ አካድኛ ጥቅም እንደ መደበኛ ወይም ይፋዊ ጽሑፍ ቋንቋ አስፋፉ።
 
በሚከተለው ዘመን በ[[ግብጽ]] የተገኙ [[የአማርና ደብዳቤዎች]] (1369-1339 ዓክልበ.) እንዳሳዩ፣ ጽሕፈት የነበራቸው አገራት ሁሉ አካድኛ እንደ መደበኛ ቋንቋ ይጠቀሙ ነበር። የ[[ጥንታዊ ግብጽ]]፣ የ[[ከነዓን (ጥንታዊ አገር)|ከነዓን]]፣ የ[[ሚታኒ]]፣ የ[[ኬጥያውያን መንግሥት]]፣ የ[[ባቢሎን]] (ካራንዱኒያሽ)፣ የ[[አላሺያ]] ወይም የ[[አርዛዋ]] ባለሥልጣናት ሁላቸው በአካድኛ ተነጋገሩ። እነዚህ አገራት ግን ለየራሳቸው ልሳናት [[ግብጽኛ]]፣ [[ከነዓንኛ]]፣ [[ሑርኛ]]፣ [[ኬጥኛ]]፣ [[ካሥኛ]]፣ [[ሚኖአንኛ]] እና [[ሉዊኛ]] ነበሩዋቸው።