ከ«ባኃኢ እምነት» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

No change in size ፣ ከ2 ዓመታት በፊት
የባሃይ ([[ፋርስኛ]]፦ /በሃኢ/ «የክብር») እምነት መነሻ ከ[[ሺዓ እስልምና]] ውስጥ ይቆጠራል። በሺዓ ውስጥ፣ እንዲሁም በፋርስ አገር ያብዛኞቹ ክፍል ውስጥ፣ «[[የአሥራሁለተኞቹ ወገን]]» ሲባሉ ይሄ ማለት የነቢዩ [[መሐመድ]] 12ኛው ተከታይ ወራሽ ወይም [[ኢማም]]፣ [[ሙሃመድ አል-ማህዲ]]፣ በ5ኛው አመተ እድሜ በ[[866]] ዓም ሳይሞት እንደ ተሰወረ፣ ወደፊትም በመጨረሻ ቀናት ለአለም ፍጻሜው ትግል፣ እርሱ ከ[[ኢሳ]] ([[ኢየሱስ]]) ጋር ይታያል የሚል የአብዛኞቹ ሺዓዎች ጽኑ እምነት ነው። ይህም እምነት በ[[እስልምና]] ትንቢቶች ላይ ይመሠረታል። «የ12ኞቹ ወገን» አማኞች እንግዲህ ከ866 ዓም ጀምረው ለዚሁ [[ማህዲ]] ዳግመና እንዲመልስ ጠብቀዋል።
 
በ[[1816]] ዓም በፋርስ፣ [[አህመድ ሻይኽ]] የተባለ መምህር የ[[ሻይኺስም]]ን እንቅስቃሴ መሠረተ፣ ይህም ወገን በተለይ የተነበየ ማህዲን ስለ ማግኘት ልዩ ትኩረት ይሰጥ ነበር። በሻይኽ አህመድ ተከታይ በ[[ሲዪድ ካዚም]] ዕረፍት በ[[1836]] ዓ.ም.፣ የሻይኺስም አማኞች በመላው ፋርስ ማህዲውን ለማግኘት ወጥተው፣ አንድ «ሲዪድ አሊ ሙሐመድ» የተባለ ወጣት አገኝተው «እኔ ለማህዲው መንፈሳዊው በር (ወይም [[ባብ]]) ነኝ» አላቸው። ሰውዬውም ከዚያ ጀምሮ «ባብ» በመባል ታውቀዋል፣ታውቆዋል፣ እንቅስቃሴውም «[[ባቢስም]]» ይባል ጀመር። ከትንሽ ጊዜ በኋላ ''ባብ'' እራሱ የተሠወረው ማህዲ እንደ ነበር ለተከታዮቹ አዋጀ፣ ከዚያም በኋላ ባብ «የአዲሱ ዘመን ነቢይ» በመጨረሻም «የአምላኩ ክስተት» መሆኑን በአዋጆች ገለጸ። ከዚህስ በኋላ የፋርስ ባለሥልጣናት ከ[[ቁርዓን]] በ[[ሺርክ]] እንደ ወጣ እንደ ረባሽ ወይም ሀረጤቃ ቆጥረውት አሠሩትና በ[[1842]] ዓም ይሙት በቃ ፈረዱበት።
 
ባብ «የአዲሱ ዘመን ነቢይ» እየተባለ፣ «የአምላኩ ክስተት ሊመጣ ነው» ስለ ነበየ፣ ከማረፉ ቀጥሎ ቢያንስ ሃያ ሰዎች ደግሞ «እኔ የተነበየው የአምላኩ ክስተት ነኝ» ብለው አሳወቁ። ሚርዛ ሁሰይን አሊ-ኑሪ፣ ወይም ባሃኦላህ ከባቢስም አማኞች አንዱ ሆኖ የፋርስ ባለሥልጣናት ካሠሩት መካከል ነበር። ከእስር ቤት ሲወጣ ከፋርስ በስደት ወደ [[ኦቶማን መንግሥት]] ተባረረ፤ በዚያም አገር የባቢስም አማኞች ቅሬታ መሪና የእምነት ጽሑፎች ደራሲ ሆነ። በ1855 ዓም ባሃኦላህ የተነበየው «የአምላኩ ክስተት» እንደ ነበር ያወራ ጀመር፣ ከዚህም በኋላ አዲሱ ሃይማኖት «ባቢስም» ሳይሆን «ባሃይ እምነት» በመባል ይታወቅ ጀመር። ባሃኦላህ ደግሞ «እኔ የአምላኩ ክስተትና የተመለሰው ኢየሱስ ክርስቶስ ነኝ» የሚሉ ደብዳቤዎች ለ[[ሮሜ]] [[ፓፓ]]፣ ለ[[ንግሥት ቪክቶሪያ]]፣ እንዲሁም ለ[[ፈረንሳይ]]፣ [[ሩስያ]]፣ [[ኦስትሪያ-ሀንጋሪ]]፣ [[ጀርመን]] ወዘተ. መሪዎች ይልክ ነበር።
8,739

edits