ከ«ኡራርቱ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
አዲስ ገጽ ፈጠረ፦ «650px|thumb|ኡራርቱ ከ852-832 ዓክልበ. በንጉሥ አራሙ '''ኡራርቱ''' በጥንት የነበረ መን...»
 
No edit summary
መስመር፡ 2፦
'''ኡራርቱ''' በጥንት የነበረ መንግሥት ሲሆን በደብረ [[አራራት]] ዙሪያ ተገኘ።
 
ስያሜው «ኡራርቱ» [[አሦርኛ]] ሲሆን ከደብረ አራራት ስም ጋር እንደ ተዛመደ ይታሥባል። በአሦርኛ ሰነዶች «ኡራርቱ»ና «[[ናይሪ]]» የሚሉት ስሞች ለዙሪያው ከ1300 ዓክልበ. አካባቢ ጀምሮ ተዝግበዋል።ተዘግበዋል። በተጨማሪ በ[[ሱመር]] አፈ ታሪክ «[[አራታ]]» የተባለ ሀገር ምናልባት 2450-2350 ዓክልበ. ይታወቅ ነበር፣ እሱም ከአሶርኛው «ኡራርቱ» ጋር ዝምድና እንዳለው የሚያስቡ አሉ። በ[[ትንቢተ ኤርምያስ]] ([[ብሉይ ኪዳን]] 600 ዓክልበ. አካባቢ) ደግሞ በ51:27 የአራራት፣ የ[[ሚኒ]] እና የ[[አሽከናዝአስከናዝ]] መንግሥታት ሲጠቅስ፣ ይህ «አራራት መንግሥት» ማለት በዚያን ጊዜ የነበረው የኡራርቱን መንግሥት ይገልጻል። በ[[ኡራርትኛ]] የመንግሥቱ ስም «'''ቢያይኒሊ'''» ተባለ።
 
ከአሦርኛ መዝገቦች እንደምናውቅ፣ ከ1300 እስከ 852 ዓክልበ. ድረስ እነዚህ ናይሪ ብሔሮች በተለያዩ ነገዶች ይኖሩ ነበር፤ በ852 ዓክልበ. የናይሪ ሕዝቦች በንጉሥ [[አራሙ]] ተባብረው የኡራርቱ (ቢያይኒሊ) መንግሥት ፈጠሩ።