ከ«ኦጦ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
No edit summary
No edit summary
 
መስመር፡ 5፦
ኦጦ በ24 ዓም በ[[ጣልያን]] ተወለደ። በሮሜ ግቢ፣ ነጉሥ [[ኔሮን]] እንደ ጎበዝ ወጣት ቆጠረው። ኔሮን ግን ሚስቱን ከቃመ በኋላ ኦጦን ወደ [[ሉሲታኒያ]] ([[ፖርቱጋል]]) እንደ አገረ ገዥ ላከው።
 
የ[[ጋሊያ ሉግዱኔንሲስ]] ([[ፈረንሳይ]]) እና [[ሂስፓኒያ ታራኮኔንሲስ]] ([[ስፔን]]) ክፍላገራት አገረ ገዦች በአመጽ ሲነሡ ኦጦም ከጸረ-ኔሮን ወገን ጋራ ተባበረ። ኔሮን ራሱን ከገደለ በኋላ የሂስፓኒያ አገረ ገዥ [[ጋልባ]] ቄሣር ሆነ።
[[ስዕል:Othon pièce.jpg|400px|thumb|left|የኦጦ መሀለቅ]]
በጥር ወር 61 ዓም የ[[ጌርማኒያ]] ሥራዊት በጋልባ ላይ አመጹበትና የጌርማኒያ አገረ ገዥ [[ዊቴሊዩስ]] ንጉሥ እንዲሆን አዋጁ። ጋልባ በሮሜ ቆይቶ አልጋ ወራሹ [[ሉኪዩስ ካልፒኒዩስ ፒሶ]] እንዲሆን ሰየመው። በዚህ ኦጦ በተለይ ተናደደ፣ አልጋ ወራሽነቱን ለራሱ መኝቶ ነበርና። የሮሜ ሥራዊት ደግሞ ኦጦን ደገፈውና በጋልባ ላይ አመጹ። ጋልባ በድካምነቱ በቃሬዛ ተሸክሞ ሲቀርብላቸው ገደሉትና ያንጊዜ ኦጦ ለአጭር ወራት በፈንታው የሮሜ ቄሣር ሆነ። መልኩ ለኔሮን ተመሳሳይነት ስለነበረው በሮሜ ዜጎች መኃል እንደ አዲሱ ኔሮን ተወደደ። የኔሮንም ሰዶማዊ «ባል» [[ስፖሩስ]] ለራሱ «አገባ»።
ከ «https://am.wikipedia.org/wiki/ኦጦ» የተወሰደ