ከ«ዶናልድ ጆን ትራምፕ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
No edit summary
መስመር፡ 1፦
Penis
{{መረጃሳጥን ሰው|ስም=ዶናልድ ትራምፕ|ስዕል=Donald Trump by Gage Skidmore 10.jpg|ባለቤት=ኢቫና ዜልኒኮቫ (ከእ.ኤ.አ 1977-1991)
ማሪያ ሜፕልስ (ከእ.ኤ.አ 1993-1999)
ሜላኒያ ኖውስ (ከእ.ኤ.አ 2005 ጀምሮ)|ልጆች=ከዜልኒኮቫ
[[ዶናልድ ትራምፕ ጁኒየር]]
[[ ኢቫንካ ትራምፕ]]
[[ኤሪክ ትራምፕ]]
ከሜፕልስ
[[ቲፋኒ ትራምፕ]]
ከኖውስ
[[ባሮን ትራምፕ]]|ሙሉ_ስም=ዶናልድ ጆን ትራምፕ|አባት=ፍሬድ ትራምፕ|እናት=ሜሪ አን ማክሊኦድ|የትውልድ ቦታ=[[ክዊንስ]] [[ኒውዮርክ ከተማ]]|የተወለዱት=እ.ኤ.አ ጁን 14 1946|ሀይማኖት=ፕሪስባይቴሪያኒዝም|ፊርማ=Donald_Trump_Signature.svg}}
'''ዶናልድ ጆን ትራምፕ '''(እ.ኤ.አ. ጁን 14 ቀን 1946 ተወለደ) አሜሪካዊ ነጋዴ ፣ ፖለቲከኛ ፣ በ[[ቴሌቪዥን]] ፕሮግራሞቹ ታዋቂ እና ለእ.ኤ.አ. 2016ቱ የ[[ዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ]]  የፕሬዚደንት ምርጫ ለ[[ሪፐብሊካን ፓርቲ]] ስያሜ እጩ ነው። የትራምፕ ኦርጋናይዜሽን ሊቀ-መንበር እና ፕሬዚደንት ሲሆን በጨዋታ እና በሆቴል ዘርፍ በተሰማራው ትራምፕ ኢንተርቴይንመንት ሪዞርትስ  ደግሞ መሥራች ነው።

በክዊንስ [[ኒው ዮርክ ከተማ]] የተወለደው ትራምፕ በሪል ስቴት ሥራ ላይ ተሰማርቶ የነበረው የፍሬድ ትራምፕ ልጅ ነው። በኮሌጅ እያለም ኤሊዛቤት ትራምፕ ኤንድ ሰንስ በተባለው ድርጅት ይሠራ ነበር። በእ.ኤ.አ. 1968 ከኮሌጅ ከተመረቀ በኋላ ያንን ድርጅት ተቀላቀለ። በእ.ኤ.አ. 1971 ደግሞ ሙሉ ሥልጣን ከተሠጠው በኋላ የድርጅቱን ስም ወደ "ዘ ትራምፕ ኦርጋናይዜሽን" ለወጠው። ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ካሲኖዎችን ፣ የጎልፍ ሜዳዎችን ፣ ሆቴሎችን እና ሌሎች በእርሱ ስም የሚጠሩ ንብረቶችን አፍርቷል። እ.ኤ.አ. ከ2005 እስከ 2015 ድረስ [[ዘ አፕሬንቲስ]] የተባለ ፕሮግራምን በ[[ኤን ቢ ሲ]] ላይ ያቀርብ ነበር።

እ.ኤ.አ. በ2000 ላይ፣ ትራምፕ ለመጀመሪያ ጊዜ ለዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንትነት ተወዳድሮ ሁለት የ[[ሪፎርም ፓርቲ]] እጩነትን አሸንፎ ነበር። በእ.ኤ.አ. ጁን 16 2015 ላይ ደግሞ ለፕሬዚደንትነት እንደሚወዳደር አሳወቀ። ይህን ጊዜ ግን የሪፐብሊካን ፓርቲን በመወከል ነው። በስደት፣ በነፃ ገበያ እና በጦር ጣልቃ ገብነት ላይ ባለው ተቃውሞ ምክንያት ታዋቂ ሆኗል። በእነኚህ አነጋጋሪ አስተያየቶቹ በመላው ዩናይትድ ስቴትስ የተቃውሞ እና የድጋፍ ሰልፎች እንዲካሄዱ ምክንያት ሆኗል። በእ.ኤ.አ. ሜይ 2016 ከሪፐብሊካን የፕሬዚደንታዊ እጩነት ውድድሮች ውስጥ 28ቱን ውድድሮች ካሸነፈ በኋላ እና የተቀሩት ተቀናቃኞቹ እነ [[ቴድ ክሩዝ]] እና [[ጆን ካሲች]] ከውድድሩ ራሳቸውን ስላገለሉ፥ ትራምፕ ለሪፐብሊካን ፓርቲ እጩ መሆኑ የተረጋገጠ ሆኗል። በእ.ኤ.አ. ከጁላይ 18 እስከ 21 በተካሄደው የ2016ቱ የሪፐብሊካኖች አገር አቀፍ ስብሰባ ላይ እጩ መሆኑ በይፋ ታውጇል።

== ቀደምት የሕይወት ታሪክ ==
ዶናልድ ትራምፕ ከ[[ኒው ዮርክ]] ከአምስቱ ቀጠናዎች አንዱ በሆነው በ[[ክዊንስ]] በእ.ኤ.አ. ጁን 14 1946 ተወለደ። ለእናቱ ሜሪ አን እና ለአባቱ ፍሬድ ትራምፕ ከአምስት ልጆች መሃል አራተኛው ልጃቸው ነበር። እናቱ የተወለደችው በ[[ስኮትላንድ]] [[ሉዊስ ኤንድ ሃሪስ]] ደሴት ላይ [[ቶንግ]] በተባለው ስፍራ ነው። በእ.ኤ.አ. 1930 በ18 ዓመቷ ዩናይትድ ስቴትስን ጎበኘች እናም ከፍሬድ ትራምፕ ጋር ተገናኘች። በእ.ኤ.አ. 1936 ትዳር ይዘው በጃማይካ ኢስቴትስ ክዊንስ መኖር ጀመሩ። በዚህም ስፍራ ፍሬድ ትራምፕ ታላቅ የሪል ኢስቴት ገንቢ ሆኖ ነበር። ዶናልድ ትራምፕ፥ ሮበርት የተባለ አንድ ወንድም፣ ሜሪአን እና ኤሊዛቤት የተባሉ ሁለት እህቶች አሉት። ፍሬድ ጁኒየር የተባለ ወንድሙ ደግሞ ከአልኮል ሱስ ጋር በተያያዘ ምክንያት ሕይወቱ አልፏል።

የዶናልድ ትራምፕ አባት ከ[[ካልሽታት]] [[ጀርመን]] በስደት ከመጡት ከ[[ፍሬድሪክ ትራምፕ|ፍሬድሪክ]] እና ከ[[ኤሊዛቤት ክራይስት ትራምፕ|ኤሊዛቤት ትራምፕ]] በ[[ዉድሄቨን ክዊንስ]] ተወለደ። ዶናልድ ትራምፕ በእ.ኤ.አ. 1976ቱ የ[[ኒው ዮርክ ታይምስ]] የሕይወት ታሪክ መዛግብት ላይ እንዲሁም በእ.ኤ.አ. 1987 በታተመው [[ዘ አርት ኦፍ ዲል]] በተሠኘው መጽሐፉ ውስጥ በተሳሳተ መልኩ ፍሬድሪክ የ[[ስዊድን]] ዝርያ እንዳለው ገልጿል። ዘ ኒው ዮርክ ታይምስ የቤተሰብ ታሪክ ጸሐፊ ነው ብሎ የጠራው የወንድም ልጅ እንዳለው ከሆነ ፍሬድሪክ ትራምፕ ይህንን አቋም ለረጅም ጊዜያት የያዘው "ብዙ አይሁዳዊያን ጓደኛሞች ስለነበሩት እና ጀርመናዊ መሆን ጥሩ ስላልሆነ ነበር" ነው ብሏል። ኋላ ግን ዶናልድ ትራምፕ በቅድመ አያቶቹ ጀርመን መሆኑን አምኖ በእ.ኤ.አ. 1999 በኒው ዮርክ ከተማ በተካሄደው በጀርመን - አሜሪካን ስቱበን ሰልፍ ላይ በግራንድ ማርሻልነት አገልግሏል።

== References ==
{{Reflist|colwidth=25em}}

[[መደብ:የአሜሪካ ሰዎች]]