ከ«1 እሽመ-ዳጋን» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

6 bytes added ፣ ከ6 ዓመታት በፊት
no edit summary
በዘመኑ መጀመርያ፣ የ[[ሑራውያን]] [[ቱሩኩ]] ጎሣ አለቃ ''ሊዳይ'' ጽኑ አመጽ በሹሻራ አገር አስነሣሣ። ክፍላገሩ በተለይ ተራራማ ስለ ሆነ፣ እሽመ-ዳጋን የአሦርን ሠራዊት ሹሻራን እንዲተው አደረገ። ከዚያ ግን ኡታን አገር አሸነፈ። በተሸነፈው አገር በኡታ ሥልጣኑን ለመጠብቅ፣ ወንድሙን ያስማሕ-አዳድ ከማሪ ወደ ኡታ እንደራሴነት አዛወረው። በስደት የኖረው የማሪ ቀድሞ ንጉስ [[ዚምሪ-ሊም]] በዚያ ዕድሉን አገኝቶ ማሪን ከያስማሕ-አዳድ ነጥቆ ወደ ዙፋኑ ተመለሰ።
 
በእሽመ-ዳጋን ዘመን፣ አሦር ከማሪ፣ ከ[[ኤሽኑና]] እና ከ[[ኤላም]] ጋራ ጦርነት ያደርግ ነበር። ስለዚህ እሽመ-ዳጋን ከበፊቱ ጠላቶች ከቱሩኩ ሕዝብ ጋር የስምምነት ውል አደረገ። የቱሩኩ አለቃ ዛዚያ ሴት ልጅ ለእሽመ-ዳጋን ወንድ ልጅ ለ[[ሙት-አሽኩር]] ታጨች። በዚህ ወቅት ደግሞ የባቢሎን ሃይል እየበረታ አሦር ከባቢሎን ወዳጅነት ተጠቀመ። ሆኖም እሽመ-ዳጋን የአባቱን ግዛት በሙሉ ሊጠብቅ አልተቻለውም። በመጨረሻ ግዛቱ የኤካላቱም፣ [[አሹር (ከተማ)|አሹር]]ና [[ነነዌ]] ከተሞች ዙሪያ ብቻ ያጠቅልል ነበር።
 
በ[[ማሪ ጽሑፎች]] እንደሚዘገብ፣ በዚምሪ-ሊም 9ኛው አመት (በ1679 ዓክልበ.)፣ ኤላማውያን እሽመ-ዳጋንን ከአገሩ አባረሩትና ወደ ባቢሎን ሸሸ። በዚያ በጽናት ታመመ። እሽመ-ዳጋን ማዕረጉን በይፋ ቢጠብቅም የሃሙራቢን ሥልጣን እንዲቀብል ተገደደ። በመሞቱም አሦር በብሔራዊ ሁከት ተያዘ፤ ልጁ [[ሙት-አሽኩር]] ይቅርና ብዙ ሌሎች ሰዎች ዙፋኑን ለመያዝ ሞከሩ። ከነዚህም [[አሹር-ዱጉል]] አገሩን ለጥቂት አመት እንዲገዛ በቃ።
 
==የዓመት ስሞች==
8,739

edits