ከ«ፖርቱጋል» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
Bot: mwl:Pertual is a featured article; cosmetic changes
መስመር፡ 26፦
በዚህ በ፲፭ኛው መቶ ዓ.ም. ላይ የ[[ቱርክ]]፣ የ[[መስኮብ]]፤ የ[[ጀርመን]]፤ የ[[እንግላንድ|እንግሊዝ]]፤ የ[[ፈረንሳይ]]ና የኤስፓኝ መንግሥታት እንደ ኃያላን መንግሥታት መቆጠራቸው አልቀረም። ነገር ግን ከነዚህ ሁሉ የፖርቱጋል መንግሥት በሌላው እንኳን ባይሆን በመርከብና አገር በመያዝ ከቀሩት ይበልጥ ነበር። የቀሩት የኤውሮፓ መንግሥታት እዚያው ወሰናቸው ላይ ገዥነታቸውን ለማጽደቅ እርስ በርሳቸው ሲጨቃጨቁ የፖርቱጋል መንግሥት ግን ደኅና ደኅና መርከቦችን አዘጋጅቶ እየላከ ከመንግሥቱና ከኤውሮፓ ርቆ የሚገኘውን የ[[አሜሪካ]]ን፤ የ[[እስያ]]ን፤ የ[[አፍሪካ]]ን አገሮች ያስመረምር ነበር። መርማሪዎቹም እነ[[ቫስኮ ደጋማ]]፤ እነ[[ፔሬዝ]]፤ እነ[[አንድራድ]]፤ እነ[[ካብራል]] በመርከብ እየሄዱ ለመከላከል ጉልበት የሌለውንና በጠባዩ ሀብት ያለበትን አገር መርምረው ሲመለሱ መንግሥቱ ወታደር በመርከብ እየላከ ብዙ አገር ያዘ።
 
በሚያዝያ ፳፩ ቀን ፲፭፻ እ.ኤ.አ. [[ፒየርፔድሮ አልቫሬዝ ካብራል]] የተባለው የፖርቱጋል መኮንን በትልቅ መርከብ ሄዶ ይን ጊዜ ለቀረው ዓለም ያልታወቀውን የ[[ብራዚል]]ን አገር አስገበረና በፖርቱጋል መንግሥት ስም ቅኝ አገር አደረገው። ከዚያም አገር በተገኘው ወርቅ መንግሥቱ ሀብታም ሆነ። እንደዚሁም የመጀመሪያ የንጉሥ እንደራሴ የተባለው [[ፍራንቼስኮ ዳልሜዳ]] ወደ [[ህንድ]] አገር ሄዶ አገሩን ያዘ። ከተማውንም በጎአ አድርጎ ህንድንም የፖርቱጋል የቄሣር ግዛት አደረገና አገር ገዥውም የንጉሥ እንደራሴ ይባል ጀመር። ከዚያም በትልቁ ውቅያኖስ ውስጥ የሚገኙትን ደሴቶች ኑቤል ጉኔንና ዛሬ [[ፊሊፒን]] የሚባለውን አገር በየጊዜው በጦር ኃይል አስገበራቸው።
 
በዚሁ አኳኋን ወደ ኢትዮጵያም እነኮቪልሐኦ ቀደም ብለው በዓፄ እስክንድር ዘመን መጥተው እንደመረመሩትና የኢትዮጵያ መንግሥት በዚያ ጊዜ በነሱ አጠራር የቄሱ የዮሐንስ መንግሥት አለ ብለው አውርተው እንደነበረ ሌላ የፖርቱጋል የጦር መርከብ በአፍሪካ ድንበር በ[[ቀይ ባሕር]] ላይም እየተመላለሰ አስቀድሞ ከያዙት ከቱርኮችና ከግብጾች እየተዋጋ አንድ ጊዜም እየተሸነፈ አንድ ጊዜም እያሸነፈ ብዙ ጊዜ ተመላለሰ። በዚህ ሁሉ ምክንያት የፖርቱጋል መንግሥት ታላቅነት በሌላው ዓለም እንደ ታወቀ እንደዚሁም ፩ኛ ትልቅ መንግሥት መሆኑ ፪ኛ ክርስቲያን መሆኑ ኢትዮጵያ ባሉት የውጭ አገር ሰዎች አፍ እየተነገረ ዝናው በኢትዮጵያ ቤተ መንግሥት ዘንድ መሰማት ቻለ።
 
== ዋቢ ምንጭ ==