ከ«ጥንታዊ ግብፅ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
መስመር፡ 42፦
 
ለዚህ ጨለማ ዘመን ፱ኛው/፲ኛው ሥርወ መንግሥት ያሉን ቅርሶች ብዙ አይደሉም። ከሥነ ቅርስ በእርግጥ የታወቁት ነገሥታት [[መሪብታዊ ቀቲ]]፣ [[ነብካውሬ ቀቲ]]ና [[መሪካሬ]] ይጠቅልላሉ። በዚህም ዘመን የተደረጀ ሥነ ጽሑፍ (''[[ትምህርት ለመሪካሬ]]'') ይታይ ጀመር።
 
በ2121 ዓክልበ. ግድም አዲስ «ጤባዊ» (፲፩ኛው) ሥርወ መንግሥት በ[[2 መንቱሆተፕ]] ተመሠረተ። ዋና ከተማው [[ጤቤስ]] በደቡብ ሲሆን በስሜኑ በሄራክሌውፖሊስ የነበረው ቀቲዎች ወገን በመሪካሪ መሪነት ዓመጹ። ለጊዜው ሁለቱ ፈርዖኖች — መሪካሬ በስሜንና መንቱሆተፕ በደቡብ — ይታገሉ ነበር። በመጨረሻ ግን መንቱሆተፕ ድል አድርጎ እንደገና መላውን ግብጽ ገዛ። ይህ መንቱሆተፕ የዙፋን ስሙን በየጊዜ የቀየረው ምክንያት ግልጽ ባይሆንም እንደ ቀድሞው ኻሰኸምዊ በመምሰል አዲስ አገር ሲገዛ አዲስ ስም እንዳወጣ ይሆናል። በግብጽ አረመኔ እምነት መንቱሆተፕ ደግሞ የትንታዊ ጣኦት [[ኦሲሪስ]] ትስብዕት ለብዙ ዘመናት ይቆጠር ነበር።
 
<references/>