ከ«2 ባርዱስ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
አዲስ ገጽ ፈጠረ፦ «'''2 ባርዱስ''' ('''ትንሹ ባርዱስ''') በ1490 ዓ.ም. አኒዩስ ዴ ቪቴርቦ የተባለው ጣልያናዊ መነኮሴ ባሳተ...»
 
No edit summary
መስመር፡ 3፦
ሎንጎ እና ልጁ 2 ባርዱስ አብረው [[ሎንጎባርዲ]] የተባለውን ወገን እንደ መሠረቱ የሚያምኑ ጸሐፊዎች አሉ። ሆኖም ሎንጎባርዲ እራሳቸው በጻፉት ታሪክ መጻሕፍት ዘንድ፣ መጀመርያ ከ[[ስካንዲናቪያ]] ወጥተው ሎንጎባርዲ ወይም «ረጅም ጺሞች» ከተባሉ በኋላ ነው በስሜን ጣልያን በ[[6ኛው ክፍለ ዘመን]] ዓ.ም. የሠፈሩ። ስለዚህ ሎንጎባርዲ ከሎንጎ እና ከባርዱስ እንዳልተሰየሙ የስሞቹም ተመሳሳይነት አጋጣሚ እንደ ሆኑ የሚጽፉም አሉ።
 
በትንሹ ባርዱስ ዘመን የ[[ኦጊጌስ]] ጐርፍ በ[[ግሪክ አገር]] ስለ ደረሰ፣ አዲስ ከተማ የኦጊጌስን ስም ለማስታወስ «ቦርግ-ኦጊጌስ» እንደ ተሠራ የሚሉ መጻሕፍት አሉ፣ ይህም የአሁን [[ቦርዥቡርዥ]]፣ ፈረንሳይ ማለት ነው። ከዚህ ሌላ ልማድ ቦርዥ በዚህ ዘመን ተሠርቶ ቢሆንም ስያሜ ከባርዱስ ስም ግንኙነት እንዳለው ይላል።<ref>[http://books.google.com/books?id=_pIOn38CJ0MC&dq=%22longho%22%20bardus&pg=RA1-PA87#v=onepage&q=%22longho%22%20bardus&f=false የ1677 ዓም ፈረንሳይኛ ታሪክ]</ref>
 
በብዙ ምንጮች ዘንድ ከባርዱስ ቀጥሎ ልጁ [[ሉኩስ]] ተከተለው። አንዳንድ መጽሐፍ ግን የባርዱስ አንድያ ልጅ [[ኬልቴስ]] ሕጻን ስለ ሆነ አካለ መጠን እስከሆነበት ወቅት ድረስ ሉኩስ በእንደራሴነት ገዛ ይለናል።<ref>[http://books.google.com/books?id=BhlDAAAAcAAJ&dq=%22longho%22%20bardus&pg=PA2#v=onepage&q=%22longho%22%20bardus&f=false የ1642 ዓም ፈረንሳይኛ ታሪክ]</ref>