ከ«ግብፅ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
r2.7.3) (ሎሌ መጨመር: gu:ઇજિપ્ત
Robot: sh:Egipat is a featured article; cosmetic changes
መስመር፡ 52፦
=== የግሪክ ጸሐፍት አፈ ታሪክ ===
 
በ6ኛው ሥርወ መንግሥት መጨረሻ [[ኒቶክሪስ]] የተባለች ሴት የአገሩ ንግሥት እንደ ሆነች የሄሮዶቶስና የማኔጦን ታሪኮች ይነግራሉ። ሄሮዶቶስ እንደሚለው፣ ወንድሙዋን ግብፆች ስለ ገደሉባት እሷም ልትበቀልለት አሰበች። ለዚሁ ጉዳይ ከመሬት ውስጥ አንድ ታላቅ አዳራሽ አሠራች። ከዚያም ታላቅ ግብር አዘጋጅታ የወንድሙዋን ገዳዮች ወደዚሁ ግብር ጠራቻቸው። የተጠሩትም በግብፅ ግዛት የታወቁ ክቡራን ነበሩ። እንዲሁ ሆኖ ሳለ በድንገት ከውጪ በራሳቸው ላይ ውካታና ፍጅት ጩኸትም ተነሳ። የጥፋት ውሃ አዳራሹን ሰብሮ ገባ። ንግሥት ኒቶክሪስ አስቀድማ የወንዙን ውሃ በሚስጥር ወደ አዳራሹ እንዲገባ አድርጋ ነበርና ውሃው በዚያ ታላቅ ግብር ላይ እንዲለቀቅ አደረገች። በዚያም የገቡ ሁሉ ሰጥመው ቀሩ። ይህ የኒቶክሪስ ታሪክ በሄሮዶቶስም ሆነ በማኔጦን ቢገኝም፣ በዘመናዊ ሥነ ቅርስ አስተያየት ለዘመንዋ ምንም ማስረጃ ስላልተገኘ አሁን እንደ አፈ ታሪካዊ ንግሥት ብቻ ትቆጠራለች።
 
በግሪኮች የታሪክ ጸሐፍት ዘንድ ሌላ ስመ ጥሩ ፈርዖን [[ሲሶስትሪስ]] ነበር። ይህ ንጉሥ ዓለምን ለማሸነፍ አስቦ ከግብፅ ሲነሣ የሚሊዮን እኩሌታ የሚሆኑ እግረኛ ወታደሮች፣ ፳፬ ሺህ ፈረሰኞች፤ ፳፯ ሺህ የተሰናዱ ሠረገሎች እንደ ነበሩት ይተረኩ ነበር። ዝና ፈላጊነቱ በክብር ተፈጸመለትና ትልቅ ድል አገኘ። በየሄደበት ስፍራ ሁሉ ከእብነ በረድ የተሠራ ሐውልት አቆመ። የሚመጣው ትውልድ እንዳይረሳው ባቆመው ሐውልት ላይ ጽሕፈት እንዲቀረጽበት አደረገ። በብዝዎቹ ሐውልት ላይ እንዲህ የሚል ቃል ተጽፎአል።
መስመር፡ 71፦
እስክንድር ሲሞት በዚሁ በእስክንድርያ ተቀበረ። ይኸው ከተማ ስመ ጥሩ በመሆኑ እስከ ዛሬ በግብፅ ዋና የንግድ ሁለተኛ ከተማ ተብሎ ይጠራል።
 
እስክንድር የሱ ጀኔራል የነበረውን ጵቶልሚዎስን አገሩን እንዲገዛ ሾመው። ከጵቶልሚዎስ ጀምሮ ተወላጆቹ ሁሉ የንጉሥ ዘር ተብለው ሁሉም ጵቶልሚዎስ ተብለዋል። ፪፻፺፬ ዓመት ገዝተዋል። ከነዚህም በመጨረሻ የነገሠው ጵቶልሚዎስ ዲዮናስዮስ ይባላል። በላዮ የገዛ ሚስቱ ተነሥታ ሸፈተችበትና ተዋጋችው። ጵቶልሚዎስ ዲዮናስዮስ በመጨረሻ ድል ሆነና ለማምለጥ የማይሆንበት ቢሆን በነጭ ዐባይ ወንዝ ውስጥ ገብቶ ሰጠመ። ሚስቱ [[ክሌዎፓትራ]] የተባለች የግብፅ ዋና ገዢ ሆነች። አሉ ተብለው ከሚጠሩት ቆነጃጅት አንዲቱ እርስዋ ነበረች። ስጦታዋና ተፈጥሮዋ ከውበትዋ ጋር የተካከሉ ነበሩ። ዳሩ ግን ክፉ ነበረች። ከሠራችው ሁሉ እጅግ የሚያሰቅቀው ነገር ያሥራ አንድ ዓመት ሕፃን የነበረውን የገዛ ወንድምዋን በመርዝ ማስገደልዋ ነው። ምንም ክፋትዋን ዓለም ቢያውቀው እኔ ነኝ ያለ ጀግና የውበት ማጥመጃዋን ሊቃወም የሚችል አልተገኘም። <sup>Whole paragraph is POV</sup>
 
[[ማርክ አንቶኒ]] የተባለ የ[[ሮማ]] ጀኔራል በግሪክ አገር [[ፊሊጵ]] በተባለች አውራጃ [[ብሩተስ]]ንና [[ካሲውስ]]ን ድል ባደረገ ጊዜ ከሜዴቴራኒያን ባሕር በሰሜን ምሥራቅ ወደምትሆን ወደ [[ሲሲሊያ]] እንድትመጣ ክሌዎፓትራን አስጠራት። ምክንያቱም ለብሩተስ ረድታ ነበርና ሊቀጣት አስቦ ነበር።
መስመር፡ 98፦
ይኸው ጨካኙ ጀኔራል አንድ ቀን ሼህ ሳዳ የሚባል አንድ ሽማግሌ እስላም አገኘና ውስጥ እግሩን በከዘራ አስደበደበው። ወዲያው ትንሽ እንደ ቆየ ጀኔራሉ ወደ መስጊድ ገብቶ ሳለ አንድ የተናደደ እስላም ገሠገሠና በጩቤ ቢሽጥበት ያን ጊዜውኑ ሞተ።
 
በ፲፰፻፩ ዓመት [[እንግሊዝ]] ፈርንሳዮችን ከግብፅ ለማስወጣት ከብዙ ጦር ጋራ ሰር [[ራልፍ አቤሮክሮምቢ]]ን ሰደደው። ጀኔራል መኑ የፈረንሳይ ኮማንደር ነበር። [[አቡኬር]] ላይ ተዋጉና ሰር ራልፍ አቤሮክሮምቢ ድል አደረገው። ዳሩ ግን እርሱም ራሱ ክፉኛ ቆስሎ ነበር።
 
በዚያው ዓመት የፈርንሳይ ጦር ተሸነፈና ከግብፅ ወጥቶ በመርከብ ተሳፍሮ ወደ ፈረንሳይ አገር ተመለሰ። ዳሩ ግን ባላገሮቹ ከፊተኞቹ ገዢዎቻቸው ከቱርኮች ይልቅ የፈረንሳይ ጀኔራል ቅን ፍርድ እየፈረደ በመልካም አገዛዝ በደንብና በሕግ ይገዛቸው ነበርና በመሄዱ እጅግ አዝነው ተላቀሱ።
መስመር፡ 133፦
[[መደብ:ግብፅ]]
[[መደብ:ስሜን አፍሪቃ]]
 
{{Link FA|sh}}
 
[[ab:Мысры]]