ከ«ዲዮኒሶስ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
r2.7.1) (ሎሌ መጨመር: bar:Dionysos
Robot: hr:Dioniz is a featured article; cosmetic changes
መስመር፡ 1፦
[[ስዕል:Dionysos kantharos BM B589.jpg|250px|thumb|ዲዮኒሶስ ጠጅ ሲያጠጣ]]
 
'''ዲዮኒሶስ''' ([[ግሪክ (ቋንቋ)|ግሪክ]]፦ Διόνυσος /ዲዮኑሶስ/) ወይም '''ባኩስ''' በጥንታዊ [[ግሪክ (አገር)|ግሪክ]] እና [[ሮማውያን]] አረመኔ ሃይማኖቶች ውስጥ የ[[ወይን]]ና የስካር አምላክ ነበረ። የ[[ዚውስ]] ልጅ ይባላል። የእናቱ ስም በምንጮቹ ይለያያል፤ ወይም ሴት አምላክ ፐርሰፎኔ፣ ወይም መዋቲ ሴት ሴሜሌ ነበረች። [[ኒሳ (አፈ ታሪክ)|ኒሳ]] በሚባል ደሴት ወይም ተራራ እንደ ታደገ ይታመን ነበር። በስሙ «ዲዮ-» የሚለው ክፍል ማለት «የዚውስ» እና «-ኒሶስ» ማለት «ከኒሳ» እንደሆነ ይመስላል።
 
በአንዱ ተውፊት ዘንድ ዚውስ ዲዮኒሶስን ከጸነሰ በሕዋላ የዚውስ ሚስት [[ሄራ]] በእናቱ ላይ እጅግ ቀናተኛ ሆነችና ልትገደለው አሰበች። ቲታኖቹን ልካ ሕጻኑን በሉት፣ ዳሩ ግን ዚውስ አጠፋቸውና ልጁን እንደገና በጭኑ ውስጥ አኖረው፤ ሁለተኛም ተወለደ። ስለዚህ ዲዮኒሶስ «ሁለት ጊዜ የተወለደው» ይባል ነበር። ዚውስ ልጁን ለ[[ሄርሜስ]] (ወይም ለሌሎች) ጥብቅና ሰጠውና በሥውር በኒሳ ታደገ። በዚያ የ[[ወይን ጠጅ]] አሠራር አገኘና የወይን ጥቅም በማስተማር ዓለሙን ዞረ። በ[[ፍርግያ]]፣ [[ሕንድ]]፤ ግሪክ አገርና ጥራክያ ተጓዘ።
 
ጸሐፊው [[ዲዮዶሮስ ሲኩሉስ]] የ[[ሊቢያ]]ን ትውፊት ሲጠቅስ፣ ዲዮኒሶስ የዚውስ [[ሃሞን]] ልጅ ሲሆን የአባቱን ቂም በቅሎ [[ክሮኖስ]]ንና [[ሬያ]]ን ያሸንፋል፤ ከዚያ የክሮኖስን ልጅ [[ዚውስ ኦሊምፖስ]]ን የግብጽ ገዥ እንዲሆን ያደርገዋል።
 
[[አኒዮ ዳ ቪተርቦ]] ያሳተመው ዜና መዋዕል እንዳለው፣ ዲዮኒስዮስ የሊቢያ ንጉሥ ሃሞንና የቁባቱ [[አልማንጤያ]] ልጅ ነው፤ የሃሞንም ሚስት ሬያ ተቆጥታ ልጁ ወደ ኒሳ በሥውር እንዲታደግ ተላከ። በኋላ ወደ ሊቢያ ተመልሶ ሬያንና ወንድምዋን [[ካም|ካሜሴኑስ]]ን (የኖኅ ልጅ ካም) አባረራቸው። ልጃቸውን ዩፒተር ኦሲሪስ የግብጽ ገዥ አደረገው። ያንጊዜ ደግሞ ዲዮኒስዮስ አንዲት ሴት ልጅ [[ፓላስ]]ን በ[[ትሪቶኒስ ሀይቅ]] አገኝቶ ለራሱ ልጅ ትሆን ዘንድ አሳደጋት።
 
[[መደብ:አፈ ታሪክ]]
[[መደብ:ግሪክ]]
[[መደብ:ሊቢያ]]
 
{{Link FA|hr}}
 
[[af:Dionysos]]