ከ«ግብረ ስጋ ግንኙነት» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
መስመር፡ 109፦
[[Image:Male and female pheasant.jpg|thumb|upright=1.1|right|የአንዳንድ አእዋፍ አይነቶች የፆታዊ አካል ልዩነት በመልክም በመጠንም አኳያ ይንፀባረቃል]]
 
ብዙ እንሥሣት በመልክም ሆነ በመጠን ልዩነት ያሳያሉ። ይህ ክስተት ፆታዊ የአካል ልዩነት (sexual dimorphism)በመባል ይታወቃል። ፆታዊ የአካል ልዩነት ከወሲባዊ ምርጠት (sexual selection)- ተመሣሣይ ፆታ ያላቸው ግላዊ ፍጡራን ከተቃራኒ ፆታ ጋር ለመዳራት የሚያደርጉት ፉክክር- ጋር የተቆራኘ ነው። የአጋዘን ቀንድ ላምሣሌ ወንዶቹ ከሴቶቹ ጋር የመዳራት እድል ለማግኘት ለሚያደርጉት ፍልሚያ ያሚያገለግል ነው። በአብዛኛው የአንድ አይነታዊ ፍጡርዝርያ የወንድ ፆታ አባሎች ከሴቶቹ በአካል ይገዝፋሉ። በአጥቢ እንሥሣት ውስጥ ክፍተኛ ፆታዊ የአካል ልዩነት ከታየ ከዚሁ ጋር ተያይዞ አንድ ወንድ ብቻውን ከብዙ ሴቶች ጋር የመዳራት ሁኔታ ይታያል። ይህም የሚሆነው በአካባቢው በሚገኙት ግላውያን ወንዶች መካከል በሚከስተው የጋለ የድሪያ መብት ማረጋገጫ ፍልሚያ ምክንያት ነው።
 
በሌሎች እንሥሣት፣ ነፍሳትንና አሦችን ጨምሮ፣ ሴቶቹ በአካል ከወዶቹ ይገዝፋሉ። ይህ ሁኔታ የድቀላ እንቁላልን ከማዘጋጀት ጋር የተያያዘ ነው ለማለት ይቻላል። ቀድም ሲል እንደተወሳው የእንስትን የዘር ቅንቁላል ወይንም ፍሬ ማዘጋጀት፣ የተባእትን የዘር ህዋስ ከማዘጋጅት ይልቅ ብዙ የንጥረነገር ቅምር ይጠይቃል። በአካል የገዘፉ እንስታን ብዙ የዘር እንቁላል መሥራት ይችላሉ። አንዳንድ ግዜ ይህ ፆታዊ የአካል ልዩነት እጅግ የበዛ ከመሆኑ የተነሳ ወንዶቹ የሴቶቹ ጥገኛ በመሆን ብቻ ተወስነው እንዲቀሩ ያደርጋል።