ከ«አፖሎ ፲፩» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
r2.7.1) (ሎሌ መጨመር: be:Апалон-11
r2.7.3) (ሎሌ መጨመር: eu:Apollo 11; cosmetic changes
መስመር፡ 1፦
[[Imageስዕል:Apollo 11 insignia.png|thumb|የአፖሎ 11 አርማ ]]
 
'''አፖሎ 11''' ለመጀመሪያ ጊዜ ሰወችን ከ[[መሬት]] ወደ [[ጨረቃ]] ለማጓጓዝ የተዘጋጀ የመንኮራኩር ሚስዮን ነው። ይህ ጉዞ የተቀናበረው በአሜሪካው የጠፈር አጥኝ ተቋም [[ናሳ]] ነበር። መንኮራኩሩ ሐምሌ16 1961ዓ.ም ከመሬት ሲመጥቅ፣ በውስጡ ሶስት ጠፈርተኞችን፣ ማለትም [[ኔል አርምስትሮንግ]]፣ [[በዝ አልድሪን]]ና [[ማይክል ኮሊንስ]]ን የያዘ ነበር። መጓጓዣ መንኮራኩሩ ጨረቃ ላይ ከ4 ቀን በኋላ ሐምሌ 20 ሲደረስ፣ በዚሁ ቀን አርምስትሮንግና አልድሪን የጨረቃን ምድር በእግራቸው በመርገጥ የመጀመሪያወቹ ሰዎች ሆኑ። ኮሊንስ ባንጻሩ በጨረቃ ከባቢ በመብረር ከላይ ይጠብቃቸው ስለነበር ጨረቃን አልረገጠም። ይህ ድርጊት በፕሬዘደንት [[ኬኔዲ]] "የሰወች ልጅን ጨረቃ ላይ አሳርፎ በሰላም መመለስ" አላማ ያሳካ ነበር።
 
== እቅድ ==
==== የመንኮራኩሩ ወደ ጠፈር መመንጠቅና ከንደገና መሬት ላይ ማረፍ ====
የአፖሎ 11 ሚሲዮን ወደ ጠፈር ሲመነጠቅ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰወች በአለም ዙሪያ በቴለቪዥናቸው ተመልክተውታል። ይህን ሚሲዮን ይዞ የተጓዘው [[ሮኬት]] [[ሳተርን ፬]] ሲባል ችቦው እየተንቀለቀለ ወደ ሰማይ ጉዞ የጀመረው [[ኬኔዲ ጠፈር ማዕከል]]፣ 1961 ዓ.ም. ነበር። .
[[Imageስዕል:Ksc-69pc-442.jpg|thumb|right|[[ሳተርን ፬]] ሮኬት ጠፈርተኞቹን ይዞ ሲሄድ]] መሬትን ከለቀቀ ከ2 ሰዓት በኋላ የጨረቃ ትዕዛዝ ማዕከልና ማረፊያ [[ሞዹሉ| ሞጅሎቹ]] ዋናውን ሮኬት ለቀው በጠፈር ጉዞ ቀጠሉ። ከ3 ቀን በኋላ ትዕዛዝ ማዕከሉና ማረፊያው ሞዱል የጨረቃን ምህዋር ተከትለው ጨረቃን መዞር ጀመሩ። ከአንድ ቀን በኋላ ማረፊያው ሞዱል ከትዕዛዝ ማዕከሉ ተላቆ ጨረቃ ላይ አረፈ። በዚህ የማረፍ ተግባር ወቅት የ[[ኮምፒውተር]] ስህተት ስለገጠመ ማረፊያው ሞዱል በኔል አርምስትሮንግ ቀጥተኛ ትዕዛዝ ስር ነበር። የሆኖ ሆኖ ለ25 ሰኮንዶች በቂ የሆነ ነዳጅ ሲቀር ማረፊያው መንኮራኩር ኔል አርምስትሮንግንና አልድሪንን ይዞ ጨረቃ ላይ በሰላም አረፈ።<ref>http://www.hq.nasa.gov/alsj/a11/a11.landing.html</ref>
 
==== ጨረቃ ምድር ላይ የተከናወኑ ስራወች ====
መንኮራኩሩ ጨረቃ ላይ እንዳረፈ የበዝ አልድሪን መጀመሪያ ተግባር ጸሎት ማቅረብ ነበር። አርምስትሮንግ ቀድሞ በመውጣ በጨረቃ ምድር ላይ የመጀመሪያው ሰው ሆነ። በዚህ ወቅት ከአፉ ነጥቆ የወጣው የመጀመሪያው ንግግር "ይህ ለአንድ ሰው ትንሽ ርምጃ ሲሆን ለሰው ልጅ ግን ታላቅ መመንጠቅ ነው" የሚል ነበር <ref>http://www.hq.nasa.gov/alsj/a11/a11.landing.html</ref>
 
[[fileስዕል:Frase de Neil Armstrong.ogg|thumb|left|የኔል አርምስትሮን የመጀመሪያ ቃላት በጨረቃ ላይ {{en}}]]
 
ለሚቀጥሉት ሁለት ሰዓታት አልድሪንና አርምስትሮንግ ፎቶ በማንሳት፣ ጽሁፍ በመጻፍና ናሙና እየቆፈሩ በመሰብሰብ ጊዜያቸውን አሳለፉ። ይህ ጉዳይ በወቅቱ በአለም ዙሪያ ለ6ሚሊዮን ሰወች ከ[[አውስትራሊያ]] ራዲዮ ጣቢይ የተላለፈ ነበር <ref>http://www.parkes.atnf.csiro.au/news_events/apollo11/pasa/on_eagles_wings.pdf</ref> [[Imageስዕል:Apollo 11 bootprint.jpg|thumb|right| የኔይል አርምስትሮንግ የእግር ኮቴ በጨረቃ]]
 
==== ጨረቃን መልቀቃቸውና ወደ መሬት መመለሳቸው ====
ጨረቃ ላይ ስራቸውን ካጠናቀቁ በኋላ ሁለቱ ጠፈርተኞች ወደ ማረፊያ መንኮራኩራቸው በመመለስ ለ7 ሰዓት ጨረቃ ላይ ከተኙ በኋላ ከላይ በኮሊንስ ወደ ሚበረው የትዕዛዝ ማዕከል ለመብረር ዝግጅት ጀመሩ። በመሃሉ አልድሪን የሞተር ማቀጣጠያ ኤሌክትሪክ ሽቦን ሳያስበው ስለቆረጠ በጨረቃ ላይ ሊቀሩ ሆነ። ኔል አርምስትሮንግ ግን እስክርቢቶውን በመጠቀም ሽቦውን በማያያዝ ጠገነ። በዚህ ሁኔታ ከጨረቃ በመፈንጠር ከላይ ከኮሊንስ ጋር በትዕዛዝ ማዕከሉ ተገናኙ።
 
እነ አርምስትሮንግ በጨረቃ ላይ በነበሩበት ጊዜ ብዙ ቁሶችን ትተው ተመልሰዋል። ለምሳሌ ከ73 የአለም መሪወች የተላለፉ መልዕክቶችን፣ የሰላምታ መልክዕት በሁሉ የመሬት ላይ ቋንቋወችና የሁለት ሰው ልጆች ስዕሎችን ትተው ተመልሰዋል። የአሜሪካንንም ባንዲራ በጨረቃ ተክለዋል።
 
ሓምሌ 24 የትዕዛዝ ማዕከሉ መሬት ላይ ሲደርስ ምናልባትም ጠፈርተኞቹ ያልታወቀ አደገኛ ቫይረስ ጨረቃ ላይ አጋጥሟቸው ሊሆን ይችላል በሚል በ[[ኳረንታይን]] ለ3 ሳምንት ከሰው ልጆች ተለይተው ተቀመጡ። ከኳረንታይን ሲወጡ፣ በርግጥም እንደ ታላላቅ ጀግኖች በተለያዩ የአለም ክፍሎች ስማቸው ተጠራ በ[[ዋሽንግተን ዲሲ]]ና በ[[ሜክሲኮ ሲቲ]] ለጠፈርተኞቹ ትልቅ ሰልፍ ሆነ።
 
== የተለያዩ ፎቶወች ==
<gallery>
Image:Apollo 11 launch.jpg| የሳተርን ፬ ሮኬት ከመጠቀ 1 ሰኮንድ በኋላ በ[[የድምፅ ፍጥነት|ድምፅ ፍጥነት]] ሲጓዝ
መስመር፡ 29፦
Image:Buzz salutes the U.S. Flag.jpg| በዝ አልድሪን የአሜሪካን ባንዲራ እጅ ሲነሳ
Image:Ap11-s69-31740.jpg| የአፖሎ 11 ጠፈርተኞች። ከግራ ወደ ቀኝ [[ኔል አርምስትሮንግ]]፣ [[በዝ አልድሪን]]፣ [[ማይክል ኮሊንስ]]
ስዕል:Normal_Ethiopian_Emperor_Attends_Apollo_11_Briefing_07151969).jpg | [[አጼ ኃይለ ሥላሴ]] ስለ አፖሎ 11 ሚሲዮን ገለጻ ሲደረግላቸው
</gallery>
 
== ማጣቀሻ ==
<references/>
 
መስመር፡ 56፦
[[es:Apolo 11]]
[[et:Apollo 11]]
[[eu:Apollo 11]]
[[fa:آپولو ۱۱]]
[[fi:Apollo 11]]