ከ«ሱመር» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
Robot: Replacing category የእስያ ታሪክ with ሱመር
Robot-assisted disambiguation: ዱሙዚድ - Changed link(s) to ዱሙዚድ፣ አሣ አጥማጁ
መስመር፡ 10፦
ጽሕፈት በመፍጠሩ የታሪክ መጋረጃ ሲከፈት፣ ሱመራውያን በደቡብ [[ሜስጶጦምያ]] (ከ[[ጤግሮስ]]ና [[ኤፍራጥስ]] ወንዞች መኃል፣ የዛሬው [[ኢራቅ]]) ይገኙ ነበር።
 
ጥንታዊው [[የሱመራውያን ነገሥታት ዝርዝር]] የያንዳንዱን ከተማ ሥርወ መንግሥት ይዘርዝራል። ከነዚህም በመግቢያው ያላቸው ነገሥታት ከ[[ማየ አይህ]] በፊት እንደ ነገሡ ይላል። እነዚህ ስሞች ትውፊታዊ ሊሆኑ ይችላል። ከሌላ [[አፈ ታሪክ]] ምንጭ የታወቀው በዝርዝሩ የተገኘ ስም የ[[ኪሽ]] ንጉሥ [[ኤታና]] ነው። ከዚያ በኋላ የ[[ኡሩክ]] መጀመርያ ነገሥታት [[ኤንመርካር]]፣ [[ሉጋልባንዳ]]፣ [[ዱሙዚድ፣ አሣ አጥማጁ|ዱሙዚድ]]ና [[ጊልጋመሽ]] ሁላቸው ከሌሎች ትውፊቶች ይታወቃሉ። ከ[[ሥነ ቅርስ]] የታወቀው መጀመርያ ስም [[ኤላም]]ን ያሸነፈው የኪሽ ንጉሥ [[ኤንመባራገሲ]] ነው። እሱ ደግሞ ''[[የጊልጋሜሽ ትውፊት]]'' በተባለ ጽሑፍ ስለሚገኝ ይህ ለጊልጋሜሽ ታሪካዊ ሕልውና ምናልባትነት መስጠቱ ይታመናል።
 
ከዚህ በኋላ የ[[ኡር]] ንጉስ [[መስ-አኔ-ፓዳ]] ኡሩክንና ኪሽንም አሸንፎ «የኪሽ ንጉሥ» የሚልን ስያሜ ወሰደ። በሚከተለውም ዘመን የሱመር ላዕላይነት ከኡር ወደ [[አዋን]] (ኤላም)፣ ከአዋንም ወደ ኪሽ፣ ከኪሽም ወደ [[ሐማዚ]] በመፈራረቅ ይዛወር እንደ ነበር መዘገቦች ይሉናል።