ከ«ግስበት» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
መስመር፡ 7፦
 
=== የኒውተን የግስበት ርዕዮት ===
: ''ለ ሒሳባዊው የኒውተን የግስበት ቀመር [[የኒውተን የግስበት ቀመር]] እሚለውላይ ገጽ ላይይመልከቱ ተብራርቷል።''
በ1645፣ [[እስማኤል ቡላይል]] የተሰኘው ፈረንሳዊ ፕላኔቶችን በፀሐይ ዙሪያ አንቆ የያዛቸው የግስበት መጠን ከፀሐይ ርቅት ጋር የተገልባጭ ስኩየር ዝምድና እንዳለው ቢገምትም በውኑ አለም ውስጥ ጉልበቱ ህልው መሆኑን ክዷል። በርግጥ [[ኢሳቅ ኒውተን]] የዚህን ተመራማሪ መጻህፍት እንዳነበበ መረጃ አለ። በተለምዶው ኢሳቅ ኒውተን ይህን ህግ አገኘ ይባላል እንጂ በርግጥም ብዙ ተማሪወች (እንደ [[ሮበርት ሁክ]]፣ [[ክሪስቶፎር ሬን]]፣ [[ቦሌር]] እና መሰሎቹ )የዚህን ህግ መኖር ከኒውተን በፊት ተረድተዋል። ኒውተን ስሙ የገነነው የህጉን እርግጠኛነት በሂስብ ስላረጋገጠ ነበር። በ1687 [[ኢሳቅ ኒውተን]] ባሳተመው መጽሐፉ ''[[Philosophiæ Naturalis Principia Mathematica|Principia]]'' ልክ እንደ ቡላይል የፀሐይን ግስበት ተገልባጭ ስኩየር ህግ ገምቷል። ሆኖም ግን ከቡላይል በተለየ መልኩ የጉልበቱን ተጨባጭ ህልውና በማመኑና በሂሳብ ቀመር በማረጋገጡ እስካሁን ዘመን ድረስ ስሙ ከግስበት ጥናት ጋር አብሮ ይነሳል።
 
ኒውተን በራሱ አንደበት ሲናገር «ለማረጋገጥ እንደቻልኩት ፕላኔቶችን በምህዋራቸው አንቆ የሚይዛቸው ጉልበት ከፀሐይ መካከለኛ ቦታ እስከ ፈለኮቹ (ፕላኔቶቹ) መካከለኛ ቦታ ድረስ ባለው ርቀት ተገልባጭ ስኩየር መጠን እየደበዘዘ ይሄዳል። እንዲሁ ጨረቃን ከመሬት ጋር አዋዶ የያዛት ጉልበት የጨረቃ መሃል ከመሬት መሃል ካለው ርቀት አንጻር እንደ ፈለኮቹና ጸሃይ ህግ ተመሳሳይ ነው » <ref>Subrahmanyan Chandrasekhar፣ Newton's Principia for the common reader፣ 2003፣ Oxford University Press
| location= Oxford(pp.1&ndash;2) </ref>
====ሒሳባዊ ቀመር ====
ሒሳባዊው የኒውተን የግስበት ቀመር [[የኒውተን የግስበት ቀመር]] እሚለው ገጽ ላይ ተብራርቷል።
[[Image:NewtonsLawOfUniversalGravitation.svg|thumb|right|300px| ቁስ 1 ግዝፈቷ መጠን ''m''<sub>1</sub> በሆን አጠገቧ ያለው ቁስ 2 ግዝፈቱ ''m''<sub>2</sub> የሆነውን በ ''F''<sub>2</sub> ጉልበት ትስባለች። ይህ ጉልበት ከሁለቱ ግዝፈቶች ብዜት ጋር ቀጥታ የሚመጣጠን ሲሆን በሁለቱ ነጥቦች መካከል ባለው ርቀት (''r'') ስኩየር መጠን እየደበዘዘ ይሄዳል። በሌላ አነጋገር የቁሶቹ ግዝፈት እየበዛ ሲሄድ የሚስቡበት ጉልበት እያደገ ይሄዳል፣ በቁሶቹ መካከል ያለው ርቀት ሲጨምር ስበታቸው እየደበዘዘ ይሄዳል። በነገራችን ላይ <nowiki>|</nowiki>''F''<sub>1</sub><nowiki>|</nowiki> እና <nowiki>|</nowiki>''F''<sub>2</sub><nowiki>|</nowiki> ምንጊዜም እኩል ናቸው። ''G'' ደግሞ የ [[ግስበት ቋሚ ቁጥር]] ነው ዋጋውም <math> G = 6.67428 \times 10^{-11} \ \mbox{m}^3 \ \mbox{kg}^{-1} \ \mbox{s}^{-2} </math> ነው። ]]