ከ«ምጽራይም» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
No edit summary
ሎሌ መጨመር: bo:མིས་རཱ་ཡིམ།; cosmetic changes
መስመር፡ 1፦
'''ምጽራይም''' ([[ዕብራይስጥ]]፦ '''מִצְרָיִם''' /ሚጽራዪም/) በ''[[ኦሪት ዘፍጥረት]]'' ምዕ. 10 መሠረት ከ[[የኖህ ልጆች|ኖህ ልጆች]] መካከል የ[[ካም]] ሁለተኛ ልጅ ነበረ። የምጽራይምም ልጆች [[ሉዲም]]፣ [[ዐናሚም]]፣ [[ላህቢም]]፣ [[ነፍታሌም]]፣ [[ፈትሩሲም]]፣ [[ከስሉሂም]]ና [[ቀፍቶሪም]] ናቸው።
 
የ«''ሚጽራዪም''» ትርጉም በዕብራይስጥ ደግሞ [[ግብጽ]] (ምሥር) አገር ነው። እንዲሁም በ[[አረብኛ]] የአገሩ ስም '''مصر''' (ምጽር) ይባላል። ስሙ ዕጅግ የቆየ መሆኑ እርግጠኛ ነው። በ[[አካድኛ]] መዝገቦች የግብጽ ስም «ሙሱር»፣ «ሙስሪ»፣ በ[[ኡጋሪት]]ም ጽላቶች «ምስርም» ተብሏል።
 
አባ [[አውሳብዮስ]] በጻፉት ዜና መዋዕል ዘንድ፣ የድሮ ግብጻዊው ባለታሪክ [[ማኔጦን]] (3ኛው ክፍለ ዘመን ዓክልበ.) ስለ ኋለኞቹ ግብጻውያን ሲጽፍ፣ ይኮሩበት የነበረው የታላቁ ጥንት ዘመን ከ[[ማየ አይህ]] አስቀድሞ እንዳለፈ፣ በኋላም በዚያው አገር ዳግመኛ ከሠፈረበት ከካም ልጅ ምጽራይም በውኑ እንደ ተወለዱ ጽፎ ነበር። ተመሳሳይ ታሪክ በ[[እስላም]] ጸሐፊዎች በግብጻዊው [[እብን አብድ ኤል-ሀከም]] እና በፋርሳውያን [[አል-ታባሪ]]ና [[ሙሐመድ ቈንዳሚር]] መጻሕፍት ሲገኝ፣ [[ፒራሚዶች]]፣ [[የጊዛ ታላቅ እስፊንክስ|እስፊንክስ]] ወዘተ. ሁሉ የተሠሩ ከጥፋት ውኃ በፊት በኖሩት ክፉ ዘሮች ሆኖ፣ ከዚያ በኋላ ግን አገሩ ለካም ተወላጅ ለምጽራይም (ማሣር ወይም መሥር) ተሠጠ ብለው ጻፉ።
መስመር፡ 11፦
ጸሓፊው [[ጊዮርጊስ ስንቄሎስ]] (800 ዓ.ም. አካባቢ) ግን ምጽራይም [[የግብጽ ቀድሞ ዘመን መንግሥት]] የመሠረተው ፈርዖን [[መኔስ]] እንደ ነበረ ገመተ።
 
== ሌሎች አጻጻፎች ==
* በ[[ግሪክ]] ትርጉም፦ Μεστράιμ /መስትራይም/
* በ''[[መጽሐፈ ኩፋሌ]]''፦ ሜስጥሮም
* በ''ኦሪት ዘፍጥረት''፣ ልዩ ልዩ [[ግዕዝ]] ቅጂዎች፦ ምሴጣሬም፣ ሴጣሬም፤ ሚጣራም፣ ምስጢየረም
 
[[መደብ:የኖህ ልጆች]]
መስመር፡ 20፦
 
[[ar:مصرايم]]
[[bo:མིས་རཱ་ཡིམ།]]
[[ca:Misraim]]
[[de:Mizraim]]